በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ቃሌ ቅድመ 1ኛ፡ 1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በ2017 በጀት ዓመት ከዚህ በታች ሎት 1 የሰራተኛ ቁርስ ካፌ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ቃሌ ቅድመ 1ኛ፣ 1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 002/2017
በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ቃሌ ቅድመ 1ኛ፡ 1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በ2017 በጀት ዓመት ከዚህ በታች ሎት 1 የሰራተኛ ቁርስ ካፌ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታው እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል፡-
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ (የቫት/VAT/ ወይም የTOT ተመዝጋቢ) የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸኋል፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት 2:30 እስከ 11፡00 በቃሌ ቅድመ 1ኛ፡ 1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 01 በመምጣት ለእያንዳንዱ ሎት አንድ መቶ (100) ብር በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ፣
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲጥአ (CPO) ብር 4000.00 (አራት ሺህ) በት/ቤቱ ስም በማዘጋጀት ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ተከታታይ የስራ ቀናት በስራ ሰዓት እስከ 11ኛው ቀን 4:00 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 8 ግዢ ክፍል በሚቀመጠው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፣
- ስርዝ ድልዝ ያለው የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፤
- የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን 4:00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በት/ቤቱ አዳራሽ ይከፈታል፣
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያውን በመሙላት ኦርጅናል ፋይናንሻል ኦርጅናል ቴክኒካል ሰነድ እና ኮፒ በተለያየ ፖስታ ኦርጅናል፣ቴክኒካል እና ኮፒ መሆኑን በመግለፅ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
- ተጫራቾች ሙሉ ስማቸውንና ፊርማቸውን በእያንዳንዱ ሰነድ ላይ በመፈረም ማቅረብ አለባቸው፤
- የዕቃ/ የአገልግሎት ዋጋ ቫትን ወይም TOT ጨምሮ ማሟላት አለባቸው፤
- ሰነዶቹ በማህተም መረጋገጥ አለባቸው፡፡
- አሸናፊው ተጫራች የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዕቃዎች ዋጋ 10% ማስያዝ ይኖርበታል፣
- ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጭ እንደሚሆኑና የጨረታ ማስከበሪያው (CPO) እንደሚወረስባቸው ማወቅ ይኖርባቸዋል፣
- ለአገር ውስጥ ተጫራቾች ጥቃቅንና አነስተኛ ድርጅት ከሆነ መጫረት የሚችሉት በተደራጁበት ምርት ውጤት ብቻ ሲሆን ከአደራጃችሁ መስሪያቤት የጨረታ ማስከበሪያው ደብዳቤ በማቅረብ በራሱ አምራች ድርጅት 3% አስተያየት የሚደረግላቸው ይሆናል፣
- አሸናፊ ድርጅት በራሳቸው እቃ የት/ቤቱ ሻይ ቤት ውስጥ በመገኘት ጥራት ያለው ምግብ መስራትና DStv መክፈል አለበት፡፡
- የዕቃ ብዛት 20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ የሚችል መሆኑን ተጫራቹ አውቆ የመጫረት ግዴታ አለበት፣
- ለአንድ እቃ ሁለት አይነት ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ አይችልም፤
- አንድ ቦታ ዋጋ ሳይሞላ የዘለለ ተጫራች ከጨረታ ውጭ ይሆናል፣
- አሸናፊው ሆኖ የሚመረጠው ድርጅት በጠቅላላ ዋጋ ዝቅተኛ ያቀረበ ነው፣
- ት/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ፡- ቃሌ ቅድመ 1ኛ ፣ 1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት አስኮ እያሱ ፀበል በአከሱም አዳራሽ 200 ሜትር ገባ ብሎ
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር ፡- 011273 17 69
የቃሌ ቅድመ 1ኛ ፣ 1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
