በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 አስተዳደር ለልደታ ጤና ጣቢያ የ2017 ዓ.ም ሎት1. የሻይ ክበብ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 570.70 አሸናፊ የሚያቀርበው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን አንስቶ እስከ 60 ቀን ድረስ የዋጋ ለውጥ ማድረግ አይቻልም ብቃት ያላቸውንና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቶች የሻይ ክበቡን አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡
በልደታ ክ/ከተማ ጤና መምሪያ የልደታ ጤና ጣቢያ
ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዥው መለያ ቁጥር-004
በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 አስተዳደር ለልደታ ጤና ጣቢያ የ2017 ዓ.ም
ሎት1. የሻይ ክበብ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 570.70
አሸናፊ የሚያቀርበው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን አንስቶ እስከ 60 ቀን ድረስ የዋጋ ለውጥ ማድረግ አይቻልም ብቃት ያላቸውንና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቶች የሻይ ክበቡን አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ፦
- በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ በመንግሥት ግሀን/ አስ/ኤጀንሲ ድረ ገፅ ላይ በአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር የተመዘገበ የቲን እና የቫት ተመዝጋቢ ይኼንኑ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ፤
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ /ሲፒአ/ ከጨረታው ሰነዳቸው ጋር አያይዞ ማቅረብ አለባቸው በካሽ ከሆነ አንቀበልም ፤
- ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ በተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ለእያንዳንዳቸው ሎት የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ልደታ ጤና ጣቢያ ቢሮ ቁጥር 30 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸው በታሸገ ኤንቨሎፕ ሳጥን ውስጥ ኮፒ እና ኦርጅናል ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በአስረኛው ቀን በ11፡00 ሰአት ታሽጎ በማግስቱ 4፡00 ሰአት ይከፈታል። ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰአት ታሽጎ ይከፈታል፡፡
- የዘገየ ጨረታና በጨረታ መከፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊልየመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ማህተም ፣ ፊርማ ፣ ለእያንዳንዱ ሎት የተሟላ ሰነድ መኖር አለበት ፤ ዋጋው የሚሞላበት ሰነድ መስሪያ ቤቱ በሰጠው የዋጋ ማቅረቢያ መሆን አለበት፡፡ እያንዳንዱ ተጫራች ቫትን ያካተተ መሆን አለበት ፡፡
- አንድ ተጫራች መወዳደር የሚችለው በገዛው ሎት ልከ ነው ማለትም አንድ ከገዛ አንድ እንጂ በአንድ ሎት 2-3 መወዳደር አይቻልም ፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ ጥያቄ ፡-
በልደታ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የልደታ ጤና ጣቢያ ከልደታ ቤተክርስቲያን ወረድ ብሎ ምርታማነት ማሻሻያ ጸበሉ ጎን
የመ/ቤቱ ስልክ ቁጥር 0115-58-20-61, 0115-58-49-66
የልደታ ክፍለ ከተማ ጤና መምሪያ የልደታ ጤና
ጣቢያ
