የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ባለ 4 (አራት) ኮኮብ የሆቴል መስተንግዶ አገልግሎት ግዥ በድጋሚ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
በድጋሚ የወጣ ባለ 4 ኮኮብ የሆቴል መስተንግዶ አገልግሎት
ግዥ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር ቤ/ል/ኮ/ግ/ጨ/013/2015
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ባለ 4/አራት/ኮኮብ የሆቴል መስተንግዶ አገልግሎት ግዥ በድጋሚ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም በዘርፉ የ2015 የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ እና ማስረጃ ኮፒ አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ በድረ ገፅ /Online/ የተመዘገቡ ድርጅቶችና ግለሰቦች ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 01 ባንቢስ አካባቢ ግሪh ትምህርት ቤት ፊት ለፊት ያለው አዲስ ህንፃ ላይ 4ኛ ፎቅ በኮርፖሬሽኑ የፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 150 (አንድ መቶ ሃምሳ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን 10,000 (አስር ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይንም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው ሚያዚያ 12 ቀን 2015 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮች በተገኙበት በኮርፖሬሽኑ የግዥ አስተዳደር ዳይሬከቶሬት ቢሮ 9ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 901 ይከፈታል።
ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ባንቢስ አካባቢ ግሪክ ት/ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው አዲስ ህንፃ
ስልክ ቁጥር 011 558 3711/ 011 558 3470
በቤቶች ልማት አስተዳደር ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን
