በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 13 ፋይናንስ ጽ/ቤት ልዩ ልዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታው ቁጥር 04/12/001/2014
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 13 ፋይናንስ ጽ/ቤት የ2014 1ኛ ዙር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ሎት1 አላቂ የቢሮ እቃዎች፣
- ሎት2 የደንብ ልብስ፣
- ሎት3 የጽዳት እቃ፣
- ሎት4 ህትመት አገልግሎት፣
- ሎት5 ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣
- ሎት6 ፈርኒቸር እቃዎች፣
- ሎት7 የመስተንግዶ አገልግሎት፣
- ሎት8 የቢሮ ጥገና የሚያገለግሉ እቃዎች፣
- ሎት9 የፈርኒቸር ጥገና ፣
- ሎት10 ኤሌክትሮኒክስ ጥገና፣
- ሎት11 የህዝብ ትራንስፖርት ኪራይ፣
- ሎት12 የጉልበት ሠራተኛ
በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
- ከላይ ከተራ ቁጥር 1-11 ለተጠቀሰው ዕቃ ወይም አገልግሎቶች በዘርፉ ሕጋዊና በዘመኑ የታደሰ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸዉ ማቅረብ የሚችል፤
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
- ቫት ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል፤
- ቲን ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል፤
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት አዲስ ከተማ ከ/ከተማ ወረዳ 13 ትራፊክ ሰፈር በሚገኘው ወረዳ 13 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በመገኘት ለእያንዳንዱ ሎት ብር 100 (መቶ ብር) በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይቻላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከተራ ቁጥር 1-6 ለተጠቀሱት እቃዎች ለእያንዳንዳቸው ብር 6,000 (ስድስት ሺህ ብር) ከተራ ቁጥር 7-11 ለተጠቀሱት የእቃ እና የአገልግሎት ስራዎች ለእያንዳንዳቸው ብር 4,000 (አራት ሺህ ብር) ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ የተረጋገጠ CPO ብቻ ከዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱ ጋር በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታዉ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ድረስ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች እያንዳንዱን የሚሸጡበትን ነጠላ ዋጋና የጠቅላላውን ዋጋ ከነቫቱ በመግለጽ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ሙሉ አድራሻቸውንና የጨረታውን አይነት በመጥቀስ አ/ክ/ከተማ ትራፊክ ሰፈር አካባቢ በሚገኘው ወረዳ 13 ፋይናንስ ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ተጫራቾች በዘርፋቸው የተጠቀሰውን ዕቃ በሙሉ መጫረት ይችላሉ።
- ሁሉም ተጫራቾች ሰነዱን ሞልተው ሲያስገቡ የዕቃውን ናሙና የማቅረብ ግዴታ አለባቸው ናሙና ካላቀረቡ ተቀባይነት የለውም።
- የጨረታ ሰነድ ማስረከበሪያ የጨረሻው ቀን በ10ኛው ቀን እስከ ቀኑ 11፡30 ሰዓት ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው በ11ኛዉ የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች በተገኙበት በፋይናንስ ጽ/ቤት ውስጥ ይሆናል።
- ቀጣዩ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን 4፡00 ሰአት ላይ ይከፈታል።
- አንድ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ማቅረብ አይችልም።
- ጨረታዉ ከተዘጋ በኋላ የሚጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት ኦይኖረውም።
- የጨረታ አሸናፊነቱ ሲረጋገጥ በግዥ ደንብና መመሪያ መሰረት በተቀመጠዉ የጊዜ ገደብ ዉል ለመዋዋል ፈቃደኛ የሆነ እና እቃውንም ለማቅረብ በግዥ ደንብና መመሪያ መሰረት በተቀመጠዉ የጊዜ ገደብ ዉል ለመዋዋል ፈቃደኛ የሆነ።
- ጨረታውን ተወዳድሮ አሸናፊው ከታወቀ በኋላ ውል ለመዋዋል ሲመጡ ያሸነፉበትን ዋጋ 10% cpo የውል ማስከበርያ አሰርተው መምጣት አለባቸው።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
- ማሳሰቢያ፡- ቋሚ እቃዎች በጽ/ቤቱ እስፔስፊኬሽን መሰረት ነዉ ግዥ የሚፈጸመው።
ስልክ ቁጥር 011-273-9940
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 13 የፋይናንስ ጽ/ቤት
