በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. መከላከያ ሚ/ር የጦር ሃይሎች ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተለያዩ እቃዎችን እና አገልግሎቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው ጋር አመታዊ ውል አስሮ መግዛት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. መከላከያ ሚ/ር የጦር ሃይሎች ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለአገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች የተመለከተውን ዕቃ/አገልግሎት
- ሎት አንድ- የልብ ህክምና አገልግሎት ግዥ ፣
- ሎት ሁለት- የዓይን ህክምና አገልግሎት ግዥ ፣
- ሎት ሦስት- የጥርስ ህክምና አገልግሎት ግዥ ፣
- ሎት አራት- የውስጥ ደዌ ህክምና እና ምርመራ አገልግሎት ግዥ ፣
- ሎት አምስት- የላቦራቶሪ ምርመራ አገልግሎት ግዥ ፣
- ሎት ስድስት- የዓይን መነፅር ፣ መያዣው እና አርቴፊሻል ዓይን ግዥ ፣
- ሎት ሰባት- የኦክስጅን ሙሌትና መለዋወጫ ግዥ ፣
- ሎት ስምንት- የተለያዩ ህክምና ማሽኖች ጥገናና ሰርቪስ አገልግሎት ግዥ ፣
- ሎት ዘጠኝ- ብራንድ መድሃኒት አቅርቦት ግዥ ፣
- ሎት አስር- ለታካሚዎች የበሰሉ ምግቦች አቅርቦት ግዥ
ለ2015 በጀት አመት እነዚህን ከላይ የተዘረዘሩ ግዥዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው ጋር አመታዊ ውል አስሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም በውድድሩ ለመሳተፍ የምትፈልጉ፡-
- የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል ፣
- ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር (website) የተመዘገቡ ስለመሆናቸው የሚገልፅ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆኑን ፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (tin no)ማቅረብ የሚችሉና ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት ) ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል።
- በተጨማሪ ይህ አዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የግዥ መለያ ቁጥር THOT2/2015 የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ቅዳሜን ጨምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ስለሚቆይ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ከላይ ለተጠቀሰው ሎቶች እያንዳንዳቸው የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በኢትዮጵያ ከታወቀ ባንክ ሲ.ፒ.ኦ. ወይም ባንክ ጋራንት በጦር ኃይሎች ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል (ARMED FORCE COMPREHENSIVE SPECIALIZED HOSPTAL) በሚል ተዘጋጅቶ መቅረብ አለበት።
- ጨረታው ከሎት 15 ጨረታው በወጣ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በዕለቱ ከጠዋቱ 4፡30 እና ሎት 6-10 በዕለቱ ከሰዓት 8፡00 ተዘግቶ 8:30 ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
ተጫራቾች ዝርዝር ዋጋቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ዋናውና ኮፒውን በየሎቱ ለየብቻ ፖስታውን በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር 011-369-2700 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
አድራሻ፡-በኢ.ፌ.ዲ.ሪ መከላከያ ሚኒስቴር ጦር/ኃ/ኮም/ስፔሻላይዝድ/ሆስፒታል
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. መከላከያ ሚ/ር የጦር ሃይሎች ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል
