በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምዕራብ አርሲ ዞን የዶዶላ አጠቃላይ ሆስፒታል ተኝተው ለሚታከሙ ህሙማን የተለያዩ የምግብ አይነቶችን የሚያቀርቡ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመስጠት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምዕራብ አርሲ ዞን የዶዶላ አጠቃላይ ሆስፒታል ተኝተው ለሚታከሙ ህሙማን ለምግብ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የምግብ አይነቶችን የሚያቀርቡ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመስጠት ይፈልጋል።
- በንግድ ዘርፉ በዘመኑ የታደሠ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የግብር ግዴታቸውን የተወጡ በጨረታው ካፈል የሚችሉ መሆኑን የሚገልፅ ከግብር ሠብሳቢ መ/ቤት የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው።
- ቲኦቲ (TOT) ተመዝጋቢ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል ጨረታውን መካፈል ይችላል።
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ለጨረታ ያቀረቡትን ሐሳብ መቀየር ወይም ማሻሻል እንዲሁም ከጨረታው ራስን ማግለል አይቻልም።
- የጨረታው ሰነድ የሚቆይበት ቀን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዓ.ም. እስከ 08/12/2014 ዓ.ም. እስከ 3፡30 ሰዓት ሲሆን ጨረታው የሚከፈትበት ዕለት 08/12/2014 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3፡30 እስከ 4፡00 ሰዓት ይከፈታል።
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያውን እና የመወዳደሪያ ሐሳባቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል።
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፈል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፦_
- ከተጠየቀው ዕቃ ውጪ የግል ዕቃ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው።
- ከዚህ በፊት በሆስፒታሎችም ሆነ በድርጅቶች ላይ የመመገብ ልምድ ኖሮት ማስረጃ ያቀረበ ይበረታታል።
- ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 022-666-1205 / 0910-05-99-60 /0911-00-60-00
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምዕራብ አርሲ ዞን የዶዶላ አጠቃላይ ሆስፒታል
