Tender Detail

Tender Details

  • Deadline17 Aug 2022, 10:37 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Catering And Cafeteria Services

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ለ2015 የትምህርት ዘመን ለእቴጌ መነን የሴቶች አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት እና ለገላን የወንዶች አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የምግብ አቅርቦት አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማግኘት ይፈልጋል



የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2015

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ ሀ. ለ2015 የትምህርት ዘመን ለእቴጌ መነን የሴቶች አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት እና ለገላን የወንዶች አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የምግብ አቅርቦት አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማግኘት ይፈልጋል።

ጨረታውን ለመጫረት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መስፈርት መሰረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።

  1. ተጫራቾች በዚህ የጨረታ ማስታወቂያ የተጠቀሰውን አገልግሎት ለማቅረብ በዘርፉ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው ፣ በጨረታ ለማሳተፍ የሚያበቃ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው።
  2. ማንኛውም ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን በባንክ የተመሰከረ (CPO) ለሎት ሀ. 50,000.00 ብር ለተጠቀው አገልግሎት ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ከቢሮአችን ከፋይናንስ ዳይሬክቶሬት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 103 በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  4. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን አሟልቶ ቴክኒካልና ፋይናንሻል ኦርጂናልና ኮፒ ፖስታ በመለየት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር ከጠዋቱ ከ2፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ በመንግስት ግዥ ዳይሬክቶሬት ለዚሁ ጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት።
  5. ጨረታው በአየር ላይ ከዋለ በ11ኛው ቀን በ3:30 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ከረፋዱ በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮው ቁጥር 104 ይከፈታል። ሆኖም ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ይከፈታል።
  6. የጨረታው አሸናፊ እንደታወቀ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ ለተሸናፊዎች ከ7 ቀናት በኋላ ይመለሳል።
  7. የጨረታው አሸናፊ በተጫራቾች መመሪያ በተጠቀሰው መሰረት የጨረታ አሸናፊነቱ በፅሁፍ በተገለፀ ከ7/ሰባት/ ቀናት በኋላ እስከ 15 ቀናት ውስጥ አስፈላጊውን የውል ማስከበሪያ ገንዘብ በማስያዝ ወዲያውኑ ወደ መንግስት ግዥ ዳይሬክቶሬቱ መጥቶ ውል መፈረም አለበት። ይህ ባይፈፅም የጨረታ አሸናፊነቱን በመሰረዝ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
  8. አሸናፊው ድርጅት ውል ከፈፀመ በኋላ በውሉ መሰረት በሚሰጠው ትእዛዝ መሰረት ለአገልግሎት ለማቅረብ ምቹ ማድረግ አለበት።
  9. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር፡ 011 122 6456

አድራሻ 6 ኪሎ ወደ ጃንሜዳ መንገድ ኦሮሚያ ፍ/ቤት ፊት ለፊት

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ

Save Tender

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል በ2019 በጀት ዓመት በ3 ሎት የተከፈሉ ግዥዎችን ለሁለተኛ ዙር በግልፅ ጨ...

READ MORE
በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ/የሐዋርያው ጴጥሮስ ት/ቤት ለ2019ዓ.ም የበጀት ዓመት ለትምህርት አገልግሎት የሚውል ቋሚ ዕቃዎች፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ አላቂ የትምህርት...

READ MORE