Tender Detail

Tender Details

  • Deadline15 Aug 2022, 1:36 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Catering And Cafeteria Services

የኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር ሰሜን ምዕራብ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት ለ2015 ዓ.ም በጀት ዓመት የካፍቴሪያ አገልግሎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታቂያ
የኢ/ገ/ሚ/ሰ/ምዕ/አ/አ//ግ/ከ/ቅ/ጽ ቤት/2015/01

የኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር ሰሜን ምዕራብ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት ለ2015 ዓ.ም በጀት ዓመት የካፍቴሪያ አገልግሎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ተቁ

የግዥው አይነት

ሎት
 

1

የካፌ አገልግሎት ከነ ሙሉ የኪችን እና ተጓዳኝ እቃው አቅርቦት ጋር።

አንድ

በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እና በጨረታ ሰነዱ መመሪያ ላይ በዝርዝር የሚቀመጠውን መስፈርቶች የምታሟሉ በጨረታው መሳተፍ ትችላላችሁ።

  • 1ኛ.በዘርፉ ንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላችሁ።
  • 2ኛ በዘርፉ የታደሰ ንግድ ስራ ፍቃድ ያላችሁ።
  • 3ኛ.የግብር ከፋይነት ሰርተፍኬት (TIN) ማቅረብ የምትችሉ።
  • 4ኛ.የቫት ተመዝጋቢነት ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ።
  • 5ኛ በጨረታ መሳተፍ እንደምትችሉና ግብር ስለመከፈላችሁ የሚገልፅ ክሊራንስ ማቅረብ የምትችሉ።
  • 6ኛ.መንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤንሲ ድረ ገፅ ላይ በአቅራቢነት ስለመመዝገቡ መረጃ ማቅረብ የምትችሉ።
  • 7ኛ ለካፌ አገልግሎት በጨረታ ሰነዱ እንድታቀርቡ የሚጠይቀውን የተለያዩ የምግብ እና የመጠጥ ማከናወኛ እቃዎችን በሚፈለው መጠንና ጥራት ማቅረብ የሚችሉ።
  • 8ኛ.መስፈርቶችን በዝርዝር በጨረታ ማስታወቂያ ጋዜጣ ላይ ማስቀመጥ ስለማይቻል በየሎቶቹ የጨረታ ሰነድ ላይ በተጫራቾች መመሪያ በዝርዝር በሚቀጥ የገምገሚያ ስፈርት እና በዚህ ጋዜጣ ላይ ከተራ ቁጥር አንድ እስከ ሰባት ያሉትን በማጣር እና ተጨማሪ በማድረግ ይሆናል።
  • 9ኛ ተጫራቾች ለጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00/አንድ መቶ ብር ብቻ/በመክፈል ወይም በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ከሆነ ካደራጃቸው አካል በጨረታ እንዲሳተፉ የሚገልፅ ደብዳቤ በማቅረብ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ቅዳሜን ግማሽ ቀን ጨምሮ በመስሪያ ቤቱ ህንፃ ወለል(ፍሎር) 8 በአካል በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  • 10ኛ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 5000.00(አምስት ሺ) በባንከ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  • 11ኛተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት እስከ 16ኛው የስራ ቀን (16ኛው ቀን ቅዳሜ ከዋለ ቅዳሜን ጨምሮ) በታሸገ ፖስታ ፋይናንሻል ሰነድ ኦርጂናል እና ኮፒ እንዲሁም ቴከኒካል ሰነድ ኦርጂናል እና ኮፒ ለየብቻ በማድረግ ለጨረታ ማስገቢያ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው እንዲሁም ናሙና ለሚያስፈልጋቸው ሎቶች የጨረታ ሳጥኑ ከመዘጋቱ በፊት ናሙና ማስገባት አለባቸው፡ ጨረታው ተጫራቾች በተገኙበት ወይም ባይገኙም በዚያኑ እለት በ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ4፡15 ስምንተኛ ፎቅ ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ይከፈታል።
  • 12ኛጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ቅዳሜን ግማሸ ቀን ጨምሮ ክፍት ሆኖ ይቆያል።
  • 13ኛ ተጫራቾች ላሸነፉበት አገልግሎት እና እቃዎች ድርጅቱ በተለያዩ ምክንያቶች የግዥ ትዕዛዙን ምንም ዓይነት የዋጋ ለውጥ ሳይደረግ 20% ከፍም ወይም ዝቅም ብሎ ትዕዛዝ ሊሰጥ ይችላል።
  • 14ኛ ተጫራቾች አሸናፊ ሆነው ለተገኙበት አገልግሎት ወይም እቃዎች ከአጠቃላይ የውል ዋጋው 10% የውል ማስከበሪያ የሚሆን በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ወይንም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና እንዲሁም Bid Bond ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
  • 15ኛድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • 16ኛ.ተጫራቾችማንኛውንምአይነትማብራሪያዎችንእናጥያቄዎችንሲኖር በደብዳቤ በማድረግ ገቢዎችሚኒስቴር ሰሜን ምዕራብ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት ልደታ ባልቻ ሆስፒታል ፊት ለፊት ካፕስቶን ህንፃ 8ኛ ፎቅ ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ማቅረብ እንዲሁም በስልክ ቁጥር ፡- 011 557 4673 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ አድራሻ- ልደታ ባልቻ ሆስፒታል ፊት ለፊት ካፕ ስቶን ህንፃ 8ኛ ፎቅ ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ። ስልክ ፡- 011 557 4673

የኢትዮጵያ ገቢ ዎች ሚኒስቴር ሰሜን ምዕራብ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት

 

Save Tender

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል በ2019 በጀት ዓመት በ3 ሎት የተከፈሉ ግዥዎችን ለሁለተኛ ዙር በግልፅ ጨ...

READ MORE
በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ/የሐዋርያው ጴጥሮስ ት/ቤት ለ2019ዓ.ም የበጀት ዓመት ለትምህርት አገልግሎት የሚውል ቋሚ ዕቃዎች፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ አላቂ የትምህርት...

READ MORE