የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት የሰራተኞች ካፍቴሪያ አገልግሎት እና የአስተዳደሩ የውስጥና የውጭ መስተንግዶ ተጫራቾችን አወዳድሮ አገልግሎት ለመስጠት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
የአዲስ ከተማ ከፍለ ከተማ አሰተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን ለአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የሰራተኞች የካፍቴሪያ አገልግሎት
- ሎት -1 የሰራተኞ ካፍቴሪያ አገልግሎት እና የአስተዳደሩ የውስጥና የውጭ መስተንግዶ፣
ተጫራቾችን አወዳድሮ አገልግሎት ለመስጠት ይፈልጋል። ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተለትን መስፈርት አሟልቶ በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።
- በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- በ2014 በጀት ዓመት የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው።
- የዘመኑን ግብር የከፈሉና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- የገንዘብና የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የምዝባ የምስክር ወረቀት /የአቅራቢ/ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ከ50,000.00 (አምሳ ሺህ ብር) በላይ ከተጫረቱ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገብበትን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ማያያዝ ይኖርባቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር ) በመክፈል የጨረታውን ሠነድ በሥራ ሰዓት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት የፍይናንስ ቡድን፤ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 605 መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ብቻ 10,000.00 ብር (አስር ሺህ ብር) በ ADDNS KETEMA SUB CITY ADMINSTRATOIN PBLIC SERVICE & HUMAN RESOURECE DEVELOPMENT OFFICE. PURCHASING, PROPERTY, ADMINISTRATION & GENERALSERVICE SUPPORTIVE PROCESS በሚል ስም በማዘጋጀት በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች በገዙት ሰነድ መሠረት የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አሥር ተከታታይ የሥራ ቀናት በተሰጠው ቢሮ ለጨረታ በተዘጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖባቸዋል።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት የሥራ ቀን በ10ኛው ቀን ከቀ 11:00 ሰዓት ተዘግቶ በ11ኛ የስራ ቀን ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 4:30 ፖስታው ይገባል። ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ቀን በ5፡00 ሰዓት ጨረታው ይከፈታል።
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ፡- 011–8-27-99-79 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል። 0912 63 08 74
አድራሻ- አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አዲሱ ህንጻ ከግሩም ሆስፒታል ከፍ ብሎ በአዲስ ከተማ ክፍል ከተማ ኦስተዳደር ፐብሊh ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት የፋይናንስ ቡድን፤ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 605
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደ ቡድን
