የካፋ ዞን የገ/ፃዲቅ ሻዎ አጠቃላይ ሆስፒታል የተኝቶ ታካሚ ምግብ አገልግሎት ግዥ ፣ የፅዳት ዕቃ እና የደንብ ልብስ ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 01/2014/2015 ዓ.ም.
በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መስተዳደር የካፋ ዞን የገ/ፃዲቅ ሻዎ አጠቃላይ ሆስፒታል 2014/2015 በጀት ዘመን ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የተኝቶ ታካሚ ምግብ አገልግሎት ግዥ ብቻ ፣ የፅዳት ዕቃ እና የደንብ ልብስ ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት፡-
- ለተኝቶ ታካሚ ምግብ አገልግሎት ግዥ ብቻ
- የፅዳት ዕቃ ግዥ
- ለደንብ ልብስ ግዥ ሆኖ
ከ1ኛ እስከ 3ኛ ተወዳዳሪዎች የሚጠበቅባቸው ቅድመ ሁኔታዎች
- የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ እና የዘመኑን የመንግሥት ግብር የከፈሉ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን ያላቸው) እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ
- በመንግሥት ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- የዕቃ አቅራቢነት ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ በጨረታው መሳተፍ ሲችሉ
- የጨረታው ሰነድ በሚገባበት ቀን ለተራ ቁጥር ሁለት እና ሦስት ናሙና በማቅረብ መጫረት የሚችልና ባሸነፈበት በአምስተኛ ቀን ውል መግባት የሚችል
- ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ ቦንጋ ገ/ፃ/ሻዎ አ/ሆስፒታል 2ኛ ፎቅ ግዥና ንብረት አ/ር ቢሮ ቁ.22 በመቅረብ የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር ለእያንዳንዱ ጨረታ 100(አንድ መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ። ለእያንዳንዱ ጨረታ ማስከበሪያ ብር 40,000.00 (አርባ ሺህ ብር) ሲ.ፒ.ኦ. በባንክ የተመሰከረ ማቅረብ እና ማስያዝ አለባቸው። የጨረታውን ሰነድ አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ ሰነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ ዋጋ በመሙላት ቦንጋ ገ/ፃ/ሻዎ አ/ሆስፒታል 2ኛ ፎቅ ግዥና ንብረት አ/ር ቢሮ ቁ.22 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ላይ ፖስታዎችን ማስገባት ይችላሉ።
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ላይ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ላይ ቦንጋ ገ/ፃ/ሻዎ አ/ሆስፒታል 2ኛ ፎቅ ግዥና ንብረት አ/ር ቢሮ ቁ.22 ተጫራቾች (ሕጋዊ ወኪሎች) በተገኙበት ይከፈታል።
- ተጫራች ያሸነፈበትን ዕቃ ሙሉ በሙሉ እስከ ገ/ፃዲቅ ሻዎ አጠቃላይ ሆስፒታል ቅጥር ግቢ በሚገኘው ግምጃ ቤት (ንብረት ክፍል) ለማቅረብ ፈቃደኛ የሆነ እና እስከ በጀት ዘመን ማለቅያ ድረስ ተቋሙ ተጨማሪ ግዥ ለመፈፀም ፍላጎት ሲያቀርብ ባሸነፈው ዋጋ ለማቅረብ ፈቃደኛ የሆነ
- የተጫራቾች ተሟልቶ አለመገኘት የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም።
- አሸናፊው ድርጅት ማሸነፉ ሲረጋገጥ ያሸነፈበትን የጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ለማስያዝ በሆስፒታሉ ስም በዝግ አካውንት ለማቅረብ ፈቃደኛ የሆነ እና ማሸነፉ ከተረጋገጠበት ቀን ጀምሮ 5(አምስት ቀናት) ቀርቦ የውል ስምምነት ለመፈፀም ፈቃደኛ የሆነ
- ተጫራቹ ተጫርቶ ያሸነፈውን ዕቃ ሙሉ በሙሉ ባሸነፈው ዋጋ በበጀት ዘመኑ የማቅረብ ግደታ አለበት።
- ጨረታው የሚከፈተው ቦንጋ ገ/ፃ/ሻዎ አ/ሆስፒታል 2ኛ ፎቅ ግዥና ንብረት አ/ር ቢሮ ቁ.22 ሲሆን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።
ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፦- 047 331 0316/047 331 2361 ያገኙናል።
የገ/ፃድቅ ሻዎ አጠቃላይ ሆስፒታል
/ካፋ ቦንጋ/
