የቦሩ ሜዳ ሆስፒታል ለ2015 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል የመድሃኒትና ላብራቶሪ ሪኤጀንት ፣ ለተኝቶ ታካሚዎች የበሰለ ምግብ ፣ የኮምፒውተርና የቢሮ ማሽን የጥገና እና ቀለም ሙሌት አገልግሎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ወይም በኮንትራት መያዝ ይፈልጋል
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የቦሩ ሜዳ ሆስፒታል ለ2015 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች የቀረቡትን ዝርዝሮች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ወይም በኮንትራት መያዝ ይፈልጋል፡፡
ስስሆነ ከዚህ በታቾ በቀረበው ሎት ዝርዝር መሰረት፡
|
|
ሎት |
ጨረታው ዓይነት |
የጨረታ ማስከበረያ |
የውድድሩ አይነት |
ምርመራ |
|
1 |
ሎት1 |
የመድሃኒትና ላብራቶሪ ሪኤጀንት ግዥ |
6000.00 CPO |
በተናጠል |
ለ6 ወር የሚቆይ |
|
2 |
ሎት2 |
ለተኝቶ ታካሚዎች የበሰለ ምግብ ግዥ |
6000.00 CPO |
በድምር |
ለ 1ዓመት የሚቆይ |
|
3 |
ሎት |
የኮምፒውተርና የቢሮ ማሽን የጥገና |
4000.00 CPO |
በድምር |
ለ 1ዓመት የሚቆይ |
- ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ለሁሉም ሎት የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው::
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆኑ ለሎት 3 አይመለከትም፡ ፡
- የግብር ከፋይ መሰያ ቁጥር (Tin) ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለሎት 1-2 ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) ለሎት 3. ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል በስራ ሰአት በሆሲፒታል ግቢ በመቅረብ ከዛሬ ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15(አስራ አምስት) ቀን ውስጥ በመምጣት መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ሰነድ ዋናው እና በስም በታሸı ኤንቪሎፕ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ወይም ቢሮ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስታወቂያው በአየር ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ መጫረቻ ሰነድ ላይ ሲሞሉ ለሁሉም ሎት ቫትን ጨምሮ መሆን ይኖርበታል፡፡ ለሁሉም ሎቶች የውለታ ማስከበሪያ በመመሪያው መሰረት ውል ይወስዳሉ፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የጨረታ ማስከበሪያ ብር ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው መሰረት ከባን በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ወይም ጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ፖስታ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ከጨረታው ሰነዱ ጋር አብሮ በቀረበው የጨረታ መመሪያ መሰረት ተገዥ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡ ንበረቶችን መረካከቢያ ቦታ ሆስፒታል ግቢ ይሆናል፡፡ ለሎት 2 የበሰለ ምግብ ለሚያቀርቡ የተጠቀሙበትን በየወሩ የመበራት ከፍያአስከ 2000 ብር የመክፍል ግዴታ ይኖርባቸዋል፡፡ እንደ አስፈላጊነቱ የመብራት ክፍያ ከጨመረ ሊጨምርም ይችላል፡፡ የእቃ ኪራይ የመከፍልም ግዴታ ይሆናል፡፡
- ሆስፒታሉ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ተጫራቾች በሚከፈትበት ቀን ቢኖሩም ባይኖሩም ከመከፈት የሚያስተጓጉል ነገር አይኖርም፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይንም በበዓል ቀን የሚሆን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ይከፈታል፡፡ በስ.ክ ቁጥር- 033 241 5005 ደውስው ይጠይቁን፡
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጤና ቢሮ
የቦሩ ሜዳ ሆስፒታል
