የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ደብረ ብርሃን ቅ/ፅ/ቤት የደንብ ልብስ፣ የመኪና ጎማ፣ ዘይትና ቅባት፣ የጽህፈትና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ግዥ
በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ የደብረብርሃን ቅ/ፅ/ቤት
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የደንብ ልብስ፣ የመኪና ጎማ፣ የተሽከርካሪ ዘይትና ቅባት፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ የደብረ ብርሃን ቅ/ፅ/ቤት የ2019 በጀት አመት ለጽ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል የደንብ ልብስ፣ የመኪና ጎማ፣ የተሽከርካሪ ዘይትና ቅባት፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃ ግዥ በሎት እና ያለ ሎት በዘርፉ የተሰማሩ ነጋዴዎችን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::
ሀ. ፕላስቲክ ቦቲ ጫማ ሎት 1
ለ. የተዘጋጁ ልብስ ሎት 2
ሐ. ብትን ጨርቅ ሎት 3
መ. ቆዳ ጫማ ሎት 4
ሠ. የመኪና ጎማ ሎት 5
ረ. የተሽከርካሪ ዘይትና ቅባት ሎት 6
ሰ. የጽህፈት መሳሪያ ሎት 7
ሸ. የደንብ ልብስ ስፌት አገልግሎት ሎት 8
ቀ. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
ስለሆነም ተጫራቾች:-
- በዘርፉ የተሰማሩ ፍቃዳቸውን ያሳደሱ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/Tin/ ነበር ያላቸውና የተጨማሪ እሴት/VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ::
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1 የተጠቀሱትንና ሌሎች የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
- በጨረታው የሚቀርበውን ሁሉንም ዝርዝር መግለጫ የደንብ ልብስ እና የሌሎች እቃዎች ዝርዝር መግለጫ/ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ::
- የጨረታ ሰነዱን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ /ቅዳሜን ግማሽ ቀን ጨምሮ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ለእያንዳንዱ ጨረታ ሰነድ በመክፈል በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ደ/ብርሃን ቅ/ጽ/ ቤት ቢሮ ቁጥር 3 መግዛት ይችላሉ::
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ ትእዛዝ /cpo/ ማስያዝ አለባቸው::
- የጨረታ ማስከበሪያ 2% የሚያሲዙት ቫትን አካቶ ነው፤ ግዥው ከብር 20000/ ከሃያ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ ኢንተርፕራይዙ TOT /3%/ የሚሰበስብ መሆኑን እናሳውቃለን::
- ተጫራቾች የጨረታ ዋጋውን በኦርጅናል ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የሚያቀርቡበትን ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ፤ ስምና አድራሻቸውን በመጻፍ ፈርመው ማህተም በማድረግ የጨረታ ፖስታውን በማሸግ በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ደብረ ብርሃን ቅ/ጽ/ቤት "የደንብ ልብስ እና ሌሎች በጨረታው የተገለጹ ግዥዎች ግልጽ ጨረታ" ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ /ቅዳሜን ግማሽ ቀን ጨምሮ/ እስከ መጨረሻው ቀን 4:00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል:: ጨረታው በዚሁ ዕለት 4:00 ሰዓት ላይ ሳጥኑ ታሽጎ በ4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት /ባይገኙም/ ይከፈታል::
- ተጫራቾች የሚጫረቱበት ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ ቫትን 15% ይጨምራል::
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- አሸናፊው ተጫራች የደንብ ልብሶቹን እና ሌሎቹን እቃዎች በራሱ ትራንስፖርት ኢንተርፕራይዙ በሚገኝበት ቦታ ድረስ ማቅረብ አለበት::
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0116375030/0932497118/ ደውለው ይጠይቁ::
በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ የደብረ ብርሃን ቅ/ፅ/ቤት
Summary
Amhara Forest Enterprise Debre Birhan Branch invites bids for plastic boots, clothing, fabric, leather shoes, vehicle tyres, lubricants, stationery, uniform tailoring and electronic items.
