የአዲስ አበባ ቃሊት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተወረሱና የኮንትሮባንድ ዕቃዎች የግልጽና የሐራጅ ሽያጭ በአክሽን ኢትዮጵያ
AA Kaliti Customs Office (አ.አ ቃሊት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት)
ሽያጭ ማስታወቂያ ቁጥር 20/2019
በአዲስ አበባ ቃሊት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተተው፣ የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የተለያዩ ንብረቶችን (የተሸከርካሪ መለዋወጫዎችን፣ሞባይሎችን፣ የሞባይል ክፍሎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣ የቤትና የቢሮ ዕቃዎችን ፣የተለያዩ የተዘጋጁ አልባሳትና ጫማዎች፣ የውበት መጠበቂያ ዕቃዎች እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን) በግልፅና በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። ከዚህ በታች በቅፁ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ለጨረታ የሚቀርቡ ንብረቶች ዝርዝር መረጃና መስፈርቶች ተዘጋጅቶ ከሀሙስ ህዳር 17/2019 ዓ.ም ጀምሮ ለተጫራቾች በአክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ (አፕሊኬሽን) ወይም www.auction.et ላይ በሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ላይ የሚታወቅ መሆኑ እንገልጸለን።
ማሳሰቢያ: ጨረታው ሙሉ በሙሉ የሚከናወነው በአክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ወይም ድህረ ገጽ ብቻ ሲሆን መተግበሪያውንም ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም www. auction.et ላይ መመዝገብ እና መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፤
በመሆኑም
- በዕቃ ግልጽና ሀራጅ ጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የፀና የንግድ ፍቃድ፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ፣የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ሰነዶች ፎቶ በማንሳት(ስካን በማድረግ) ኦንላይን የአክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ ወይም www.auction.et ማያያዝ ይኖርበታል።
- በጨረታው ላይ የዕቃው : አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰቡ የነበሩ ሰዎች መሣተፍ አይችሉም::
- ተጫራቾች የዕቃዎቹን ጨረታ ሰነድ ከሀሙስ ህዳር 17/2019 ዓ.ም ጀምሮ በማንኛውም ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በኦንላይን አክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ (አፕሊኬሽን) ወይም www.auction.et ላይ በመክፈል የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ::
- በዕቃ ግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ለጨረታ ማስከበሪያ (CPO) በቅ/ጽ/ቤቱ አድራሻ ስም CUSTOMS COMMISSION ADDIS ABABA KALITY CUSTOMS BRANCH OFFICE በባንክ አሰርተው ያሰሩትንም ሲ.ፒ.ኦ. በአካል ወደ አክሽን ኢትዮጵያ ቢሮ ሄደው ወይም ቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ሄደው በማስያዝ ወይም በኦንላይን አክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ::
- የዕቃ ሐራጅ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ ለዕቃዎች ብር 200,000.00 የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) በተ.ቁ 4 በተገለጸው አድራሻ ተጫራቹ ማስያዝ አለበት::ነገር ግን በዕቃ ሐራጅ በጨረታ ሰነድ ላይ በሚገለጹ የተወሰኑ ዕቃዎች ላይ የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) መጠን የሚወሰን መሆኑን እንገልጻለን:: ያሰሩትንም ሲ.ፒ.ኦ. በአካል ወደ አክሽን ኢትዮጵያ ቢሮ ሄደው ወይም ቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ሄደው በማስያዝ ወይም በኦንላይን አክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።
- ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (ስኬጁል) መሰረት መጫረት ይችላሉ።
ተ.ቁ የቅ/ጽ/ቤቱ ስም የጨረታው አይነት የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታ ሰነድ ከወሰዱ ቀን ጀምሮ የጨረታው የመዝጊያ ቀንና ሰዓት 1 አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የእቃ ሀራጅ እስከ 21/03/2019 እስከ 22/03/2019 (ከ4:00 ሠዓት ጀምሮ ኦንላይን ላይ ለየምድቦቹ በተሰጠው ጊዜ) መሠረት ይካሄዳል። 2 የእቃ ግልፅ እስከ 22/03/2019 በ23/03/2019 3:45 ላይ በኦንላይን ይዘጋል:: - የጨረታው መከፈቻ ቦታ:- ሙሉ በሙሉ የአክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ ወይም www.auction.et (በኦንላይን) የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ የጨረታውን ሂደት በኦንላይን መከታተል ይችላሉ::
- ተሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (CPO) የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል::
- አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውንና ተሸከርካሪውን ማንሣት ይኖርባቸዋል::
- ከላይ በተ/ቁ 9 በተገለፁት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክበ ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበርያ ያስያዙት እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል::
- መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
የአክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ መረጃ ለማግኘት በስልክ ቁጥር 09 - 05 -11 -55 -11
አድራሻ:- ቦሌ አትላስ አውሮፓ ህብረት ዝቅ ብሎ ከለላ ህንጻ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 301 (አክሽን ኢትዮጵያ)
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር:- አዲስ አበባ ቃሊት ጉምሩክ - 011 - 470 - 85- 03
አድራሻ:- ሳሪስ አቦ ቤ/ክ በቀለበት መንገድ ወደ ማሰልጠኛ በሚወስደው ወደ ኮዬ ፈጬ መንገድ መንገጠያ ፊት ለፊት ያለው ህንጻ
