Tender Detail

Tender Details

  • Company በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የምርጥ ዘር አቅርቦት ዘርፍ
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 6 18 61 25
  • Website
  • Deadline09 Dec 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document Priceብር 500.00 (የማይመለስ)
  • Bid Securityየጠቅላላ ዋጋውን ከ2% ያላነሰ (CPO)
  • opening dateህዳር 30 ቀን 2019 ዓ.ም ከሰዓት 8:30 ሰዓት
  • Sector Agriculture and Farming , Agricultural Products and Services , Sales

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የምርጥ ዘር አቅርቦት ዘርፍ የተፈጥሮ ሙጫ ምርቶች ሽያጭ

በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የምርጥ ዘር አቅርቦት ዘርፍ

Add to calendar Google Calendar Download .ics

የተለያዩ ዓይነትና ደረጃ ያላቸው የተፈጥሮ ሙጫ ምርቶች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ኢግስኮ - የም/ዘ/አ/ዘ/ግጨ/ሽ02/2019

በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን-የምርጥ ዘር አቅርቦት ዘርፍ በአዳማ ቅርንጫፍ የተለያዩ ዓይነትና ደረጃ ያላቸው የተፈጥሮ ሙጫ ምርቶች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል። ስለሆነም በዘርፉ የተሰማራችሁና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ሁሉ በጨረታው መሳተፍ ይችላል።

  1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላችሁና፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክርነት ወረቀት፤ የንግድ ምዝገባ የምስክርነት ወረቀት፤ በጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ የምስክርነት ወረቀት(ክሊራንስ) ኮፒ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት።
  2. ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ከ2% ያላነሰ በባንክ የተመሰከረ CPO በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የምርጥ ዘር አቅርቦት ዘርፍ ስም ከሚያቀርቡት የጨረታ ሰነዶች ጋር በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ ለ30 ቀናት የፀና መሆን ይኖርበታል።
  3. ማንኛውም ተጫራች የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የሚጠይቀውን በሙሉ አሟልቶ ማቅረብ ይጠበቅበታል። የዕጣን ምርቶች ሽያጭ ተጫራቹ በሚሰጠው ዋጋ ላይ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ ይጨመራል።
  4. ብቁ ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የተሟላ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (ብር አምስት መቶ) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መክፈቻ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ሀሙስ፣ ከሰዓት በፊት ከ2:00-6:00 ከሰዓት በኋላ ከ7:00-10:30 ፤ ዓርብ ከሰዓት በፊት ከ2:00-5:30 ከሰዓት በኋላ ከ7:30-10:30 እንዲሁም ቅዳሜ ከሰዓት በፊት ከ2:00-6:00 ሰዓት በዘርፍ ጽ/ቤት ቃሊቲ ጉምሩክ ፊት ለፊት በምርጥ ዘር አቅርቦት ዘርፍ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 206 እንዲሁም በአዳማ ከተማ መብራት ኃይል ንግድ ምክር ቤት ጎን አዳማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
  5. ጨረታው ህዳር 30 ቀን 2019 ዓ.ም ከሰዓት 8:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ህዳር 30 ቀን 2019 ዓ.ም ከሰዓት 8:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዋናው መ/ቤት በምርጥ ዘር አቅርቦት በዘርፉ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 110ና በኮርፖሬሽኑ አዳማ ቅ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 06 በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
  6. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ከቀረበው ዝርዝር ምርቶች ውስጥ በሙሉ ወይም በከፊል መጫረት ይቻላሉ።
  7. ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።
  8. ዘርፉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አዲስ አበባ 0114-70-84-75/0116-66-23-90
አዳማ 0221-11-21-22/0221-11-31-56
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የምርጥ ዘር አቅርቦት ዘርፍ

Summary
Ethiopian Agricultural Businesses Corporation Seed Supply Sector invites bids to buy various types and grades of natural gum and resin products at its Adama branch, as-is.
Save Tender Remind me on Telegram
Report a problem with this tender