የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዳማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የተወረሱ አዳዲስ አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች፣ ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎችና የኮንስትራክሽን ዕቃዎችን በ7 ምድብ በአክሽን ኢትዮጵያ በኦንላይን ባሉበት ሁኔታ ለመሸጥ ያወጣው ግልጽ ጨረታ (ቁጥር ግ-09/2019)።
የአዳማ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ ግልፅ ጨረታ
ቁጥር ግ-09/2019 ዓ.ም
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ብዛት ያላቸው ኤሌክትሮኒክስ፣ ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች፣ አዳዲስ አልባሳት (ቦርሳዎች፣ ሚማዎች)፣ የኮንስትራክሽን እቃዎች እና ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች በግልፅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ማሳሰቢያ፡- ጨረታው ሙሉ በሙሉ የሚከናወነው በአክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ብቻ ሲሆን መተግበሪያውንም ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም www.acton.et ላይ መመዝገብ እና መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
በዚህም መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶች የምታሟሉ ግለሰቦችም ሆነ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡-
- ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ክሊራንስ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ኮፒ በአክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ማንኛውም ተጫራች 100 ብር በመክፈል ከአክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ የጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- በተራ ቁጥር 1 ላይ የተጠቀሱት መስፈርቶች ቢኖርም መነሻ ዋጋቸው ከ500,000 (አምስት መቶ ሺህ) ብር በታች የሆኑ ዕቃዎችን ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አያስፈልግም፡፡
- በግልፅ ጨረታ ላይ የወጡትን ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች ማንኛውም ዕድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ ቅድመ ሁኔታዎችን ማሟላት ሳያስፈልገው በብሄራዊ መታወቂያ ብቻ የአክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብሎ በማውረድ ወይም (aucton.et) ላይ መመዝገብ እና መጫረት ይችላል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ የዕቃዎቹን ዝርዝር፣ ዓይነት እና ብዛት የያዘውን ሰነድ በአክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ ማግኘት ይቻላል፡፡ ተጫራቾች ዕቃዎቹን ከአዳማ ቅ/ጽ/ቤት ከሰኞ እስከ አርብ ሙሉ ቀን በስራ ሰዓት እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2:00-6:00 ሰዓት መመልከት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የሚወጣበት ቀን እና ጨረታው የሚዘጋበት ቀን እና ሰዓት የሚያሳይ ሰንጠረዥ፡-
ተ.ቁ የዕቃው አይነት የጨረታው ዓይነት በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የሚወጣበት ቀን ጨረታው የሚከፈትበት/የሚዘጋበት ቀን ጨረታው የሚዘጋበት ሰዓት ጨረታው የሚከፈትበት ሰዓት ስልክ ቁጥር 1 አዳዲስ አልባሳት (ቦርሳዎች) ግልፅ 16/03/2019 23/03/2019 4:00 4:30 0222118925 / 0222118429 2 ኤሌክትሮኒክስ ግልፅ 16/03/2019 23/03/2019 4:00 4:30 0222118925 / 0222118429 3 አዳዲስ አልባሳት ግልፅ 16/03/2019 23/03/2019 4:00 4:30 0222118925 / 0222118429 4 አዳዲስ አልባሳት (ሚማዎች) ግልፅ 16/03/2019 23/03/2019 4:00 4:30 0222118925 / 0222118429 5 ተሽከርካሪ መለዋወጫ ግልፅ 16/03/2019 23/03/2019 4:00 4:30 0222118925 / 0222118429 6 ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች ግልፅ 16/03/2019 23/03/2019 4:00 4:30 0222118925 / 0222118429 7 የኮንስትራክሽን እቃዎች ግልፅ 16/03/2019 23/03/2019 4:00 4:30 0222118925 / 0222118429 - በግልፅ ጨረታ ሽያጭ ላይ የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች እና ቤተሰቦቻቸው መሳተፍ አይችሉም፡፡
- በግልፅ ጨረታ የሚሳተፉ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ለእያንዳንዱ ምድብ እቃዎች እና ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተመሰከረ (CPO) (customs commission Adama Branch) ስም ብቻ ሲ.ፒ.ኦ. በማሰራት ያሰሩትን ሲ.ፒ.ኦ. በአካል ወደ አክሽን ኢትዮጵያ ቢሮ ሄደው በማስያዝ ወይም በኦንላይን አክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በማስያዝ የሚጫረቱበትን ዋጋ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- በግልፅ ጨረታ ለመሸጥ የወጡት እቃዎች እና ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች በአዳማ ከተማ በራሺ አካባቢ መ/ቤቱ በተከራየው የመንግስት ጉምሩክ መጋዘን ቁጥር 1 እና 2 ውስጥ የሚገኙ ሲሆን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ በስምንተኛው ቀን 4:00 ሰዓት ጨረታው ይዘጋል፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት CPO ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር ተደምሮ የሚታሰብላቸው ሲሆን፣ ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ3 /ሶስት/ የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በማስታወቂያ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ከላይ በተ/ቁ 10 ላይ በተገለፁት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት (CPO) ለመንግስት ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
- ለጨረታ የቀረቡት እቃዎች እና ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች ሽያጫቸው የሚፈፀመው ባሉበት ሁኔታ ስለሆነ ተጫራቾች ሌላ ተመሳሳይ ወይም ተጨማሪ ዕቃ መጠየቅ አይችሉም፡፡
- ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለጨረታ ማስከበሪያ የሚታሰሩት CPO የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ መሆን እንዳለበት እና የሌላ ባንክ የማንቀበል መሆኑን እናሳስባለን፡፡
የአክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በስልክ መስመር 05-11-5511 / 011-66-08-828 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ አዳማ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የመንግስት ጉምሩክ መጋዘን የስራ ሂደት ስልክ ቁጥሮች 0221116429 እና 0222118925 ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት
Summary
Ethiopian Customs Commission Adama Branch sells confiscated goods as is through the Auction Ethiopia online platform: new clothing and bags, electronics, vehicle spare parts, used motorcycles and construction items, in 7 groups.
