የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የምርጥ ዘር አቅርቦት ዘርፍ (አዳማ ቅርንጫፍ) የተለያዩ ዓይነትና ደረጃ ያላቸውን የተፈጥሮ ሙጫ ምርቶች ባሉበት ሁኔታ ለመሸጥ ያወጣው የሽያጭ ጨረታ (ቁጥር ሽ02/2019)።
Ethiopian Agricultural Business Corporation Seed Supply Sector
የተለያዩ ዓይነትና ደረጃ ያላቸው የተፈጥሮ ሙጫ ምርቶች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ኢግስኮ-የም/ዘ/አ/ዘ/ግጨ/ሽ02/2019
በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን-የምርጥ ዘር አቅርቦት ዘርፍ በአዳማ ቅርንጫፍ የተለያዩ ዓይነትና ደረጃ ያላቸው የተፈጥሮ ሙጫ ምርቶች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በዘርፉ የተሰማራችሁና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ሁሉ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክርነት ወረቀት፣ የንግድ ምዝገባ የምስክርነት ወረቀት፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ የምስክርነት ወረቀት (ክሊራንስ) ኮፒ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ከ2% ያላነሰ በባንክ የተመሰከረ CPO በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የምርጥ ዘር አቅርቦት ዘርፍ ስም ከሚያቀርቡት የጨረታ ሰነዶች ጋር በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ ለ30 ቀናት የፀና መሆን ይኖርበታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የሚጠይቀውን በሙሉ አሟልቶ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡ የዕጣን ምርቶች ሽያጭ ተጫራቹ በሚሰጠው ዋጋ ላይ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ ይጨመራል፡፡
- ብቁ ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የተሟላ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (ብር አምስት መቶ) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መክፈቻ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ሀሙስ፣ ከሰዓት በፊት ከ2:00-6:00 ከሰዓት በኋላ ከ7:00-10:30፣ ዓርብ ከሰዓት በፊት ከ2:00-5:30 ከሰዓት በኋላ ከ7:30-10:30 እንዲሁም ቅዳሜ ከሰዓት በፊት ከ2:00-6:00 ሰዓት) በዘርፉ ጽ/ቤት ቃሊቲ ጉምሩክ ፊት ለፊት በምርጥ ዘር አቅርቦት ዘርፍ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 206 እንዲሁም በአዳማ ከተማ መብራት ኃይል ንግድ ምክር ቤት ጎን አዳማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ህዳር 30 ቀን 2019 ዓ.ም ከሰዓት 8:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ህዳር 30 ቀን 2019 ዓ.ም ከሰዓት 8:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዋናው መ/ቤት በምርጥ ዘር አቅርቦት በዘርፉ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 110ና በኮርፖሬሽኑ አዳማ ቅ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 06 በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ከቀረበው ዝርዝር ምርቶች ውስጥ በሙሉ ወይም በከፊል መጫረት ይቻላል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
- ዘርፉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አዲስ አበባ 0114-70-84-75/0116-66-23-90
አዳማ 0221-11-21-22/0221-11-31-56
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን
የምርጥ ዘር አቅርቦት ዘርፍ
Summary
Ethiopian Agricultural Works Corporation, Seed Supply Sector (Adama branch), sells natural gum and incense products of various types and grades as is. Buyers may bid for all or part of the items; 15% VAT is added to incense prices.
