Tender Detail

Tender Details

  • Company በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251112730852
  • Websitehttps://www.fsc.gov.et/
  • Deadline25 Dec 2026, 2:00 PM
  • magazineAddis Zemen
  • CountryEthiopia
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityየመነሻ ግምት 1/4ኛ ብር 2,812,500 (CPO፣ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
  • opening dateNot stated in the notice
  • Sector Foreclosure , Sales

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት በአዋሽ ፐብሊክ ኮኔክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር የሚገኝ አክሲዮን የሐራጅ ሽያጭ (በድጋሚ)

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት

Add to calendar Google Calendar Download .ics

ድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለመብት ጀሚላ መሀመድ እና የፍ/ባለዕዳ ያሲን አብዱራህማን መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/300535 በ30/03/2017 ዓ/ም እና በፌ/ከ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ/335434 በ08/04/2018ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ፍርድ ያረፈበት በፍርድ ባለዕዳ አቶ ያሲን አብዱራህማን ስም ተመዝግቦ የሚገኝ በአዋሽ ፐብሊክ ኮኔክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር ውስጥ የሚገኝ 11,250 ( አስራ አንድ ሺህ ሁለት መቶ ሃምሳ) የሆኑ አክሲዮን የአንዱ አክሲዮን ዋጋ 1000 (አንድ ሺህ) የጠቅላላው የአክሲዮን ዋጋ 11,250,000 (አስራ አንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ) ሆኖ የስም ማዛወሪያ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ በየካቲት 6 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ለመሸጥ ቀጠሮ የተያዘ ቢሆንም በዕለቱ ተጫራች ባለመቅረቡ ምክንያት ጨረታው ሳይከናወን ቀርቷል። ስለሆነም በፌ/ከ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.335435 በቀን መጋቢት 21 ቀን 2018 ዓ.ም በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት 1/4ኛ ብር 2,812,500 (ሁለት ሚሊዮን ስምንት መቶ አስራ ሁለት ሺህ አምስት መቶ) በማስያዝ መሳተፍ የሚቻል ሆኖ የስም ማዛወሪያ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ታህሳስ 16 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 8:00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3:30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። 1/4ው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም C.P.O አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ_ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።

ለበለጠ መረጃ:-
በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት

Summary
The Federal Courts Judgment Execution Office re-advertises the court-ordered auction of shares registered in a judgment debtor's name in Awash Public Connection PLC.
Not stated in the notice: opening date, bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender Remind me on Telegram
Report a problem with this tender