Tender Detail

Tender Details

  • Company Addis Ababa University
  • Address , Phone: +251011243290
  • Website
  • Deadline14 Dec 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document Price200(ሁለት መቶ ብር)
  • Bid Securityሎት 1 ብር 10,000፣ ሎት 2 ብር 10,000፣ ሎት 3 ብር 3,000 (CPO ወይም የባንክ ዋስትና)
  • opening dateታህሳስ 5 ቀን 2019 ዓ.ም ጠዋት 4:30 ሰዓት
  • Sector Steel, Metals And Aluminium , Disposal Sale , Used Items

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ያገለገሉ ቁርጥራጭ ብረቶችን፣ ንቃይ የቤርጋ እና የጣራ ቆርቆሮዎችን እንዲሁም የሚወገድ ተሽከርካሪ በ3 ሎት ለመሸጥ ያወጣው ግልጽ የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ (ቁጥር AAU/NCB/pdi/11/2019/26)።

Addis Ababa University

Add to calendar Google Calendar Download .ics

ግልጽ የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

ግልጽ ጨረታ ቁጥር፡-AAU/NCB/pdi/11/2019/26

ሎት1፡- ያገለገሉ ቁርጥራጭ ብረቶች ሎት2፡-ንቃይ የቤርጋ ቆርቆሮ እና ንቃይ የጣራ ቆርቆሮ ሎት3፡-የሚወገድ ተሽከርካሪ ሽያጭ ጨረታ

  1. አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ያገለገሉ ቁርጥራጭ ብረቶችን እና የሚወገድ ተሽከርካሪ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
  2. አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሎት1፡-ያገለገሉ ቁርጥራጭ ብረቶች፣ በሎት2፡-ንቃይ የቤርጋ ቆርቆሮ እና ንቃይ የጣራ ቆርቆሮ፣ በሎት3፡- የሚወገድ ተሽከርካሪ ሽያጭ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡ ስለዚህ ለመግዛት ፍላጎትና ብቃት ያላቸዉ ተጫራቾች በታሸገ ኢንቨሎፕ የጨረታ ሰነድ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ እንድታቀርቡ ተጋብዛችኋል።
  3. ጨረታው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ግዥና ንብረት አስተዳደር መመሪያ ሥነ-ሥርዓት መሰረት ይፈፀማል።
  4. ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ከዚህ በታች በተራ ቁጥር 7 (ሀ) በተገለፀው አድራሻ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በዩኒቨርሲቲዉ የኢትዮጲያ ንግድ ባንክ አካዉንት ቁጥር 1000087392067 ገቢ በማድረግና ደረሰኙን ይዘዉ በመቅረብ ስለእቃዎቹ ሙሉ ዝርዝር የያዘውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።
  5. የጨረታ ሰነዱን ከዚህ በታች በተራ ቁጥር 7 (ለ) በተገለጸዉ አድራሻ እስከ ታህሳስ 5 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ ጠዋቱ 4:00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ። ዘግይተዉ የሚቀርቡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸዉም። ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቁጥር 7 (ሐ) በተጠቀሰዉ አድራሻ ታህሳስ 5 ቀን 2019 ዓ.ም ጠዋት 4:30 ሰዓት ይከፈታል።
  6. ተጫራቾች ከዚህ በታች በተራ ቁጥር 7 (ለ) በተገለጸዉ አድራሻ ታህሳስ 5 ቀን 2019 ዓ.ም ጠዋት 4:00 ሰዓት ወይም በፊት በግዥ እና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ የጨረታ ሰነዱን ከጨረታ መዝጊያ ጊዜ በፊት ማቅረብ አለባቸዉ። ተጋባዥ ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ብር ለሎት1፡-ያገለገሉ ቁርጥራጭ ብረቶች 10,000.00( አስር ሺ ብር ) ለሎት2፡-ንቃይ የቤርጋ ቆርቆሮ እና ንቃይ የጣራ ቆርቆሮ 10,000.00( አስር ሺ ብር ) ለሎት3፡-የሚወገድ ተሽከርካሪ 3,000 .00(ሶስት ሺ ብር ) በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በዩኒቨርሲቲዉ ስም አሰርተዉ አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ። በተጨማሪም ጨረታዉ ከተከፈተ በኋላ ማንኛዉም ተጫራች ከዉድድሩ ከወጣ የተያዘዉ የጨረታ ማስከበሪያ የሚወረስ ይሆናል።
  7. ሀ/ ሰነዶቹ የሚሸጡበት አድራሻ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 314
    ለ/ የጨረታዉ ሰነድ የሚገባበት አድራሻ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 200
    ሐ/ ጨረታዉ የሚከፈትበት አድራሻ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 200
  8. የጨረታ አሸናፊዉ ድርጅት ወይም ግለሰብ የዉል ስምምነት ላይ በሚገለፀው ቀን መሰረት ለዩኒቨርሲቲዉ ሙሉ ክፍያ በመፈጸም ከከፈለበት ቀን ጀምሮ ባሉት በ10 ተከታታይ ቀናት ውሥጥ ያሸነፈበትን እቃ ማንሳት አለበት።
  9. ዩኒቨርሲቲዉ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታዉን የመሰረዝ መብት አለዉ።

ስልክ ቁጥር፡- 011-122-00 01/011-124:32-72 ፖ.ሣ.ቁ 1176

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ

Summary
Addis Ababa University sells used scrap metal (Lot 1), dismantled corrugated iron sheets and roofing (Lot 2) and a vehicle for disposal (Lot 3) by sealed bid. Winners must pay in full and collect within 10 days.
Save Tender Remind me on Telegram
Report a problem with this tender