Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Petroleum Supply Enterprise(EPSE) (የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት)
  • Address ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ ሳርቤት በሚወስደው መንገድ 300 ሜትር ዝቅ ብሎ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0115512938
  • Websitehttps://epse.gov.et/
  • Deadline22 Dec 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document Price300(ሶስት መቶ ብር)
  • Bid Securityምድብ 1 ብር 50,000፣ ምድብ 2 ብር 40,000 (CPO ወይም የባንክ ጋራንቲ)
  • opening dateታህሳስ 13/2019 ዓ.ም 4:05 ሰዓት፣ ቢሮ ቁጥር 602
  • Sector Steel, Metals And Aluminium , Construction Materials And Raw Materials , Sport Materials And Sportswear

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት የልጆች የውጭ መጫወቻ ሜዳ መሳሪያዎች እና የተለያዩ የግንባታ እቃዎች (ሲሚንቶ፣ ብረት፣ ጣውላ፣ ጥቁር ሽቦና ሚስማር) ግዥ በ2 ምድብ ያወጣው የጨረታ ማስታወቂያ (ቁጥር 13/2019)።

Ethiopian Petroleum Supply Enterprise(EPSE) (የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት)

Add to calendar Google Calendar Download .ics

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡ 13/2019

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ምድብ 1፡- Equipment for Children Outdoor-Playground
ምድብ 2፡- Various Construction Materials (Cement; Reinforcement bar; Timber; Black Wire and Nails)

ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች ማሟላት የሚችሉ ድርጅቶች መወዳደር ይችላሉ።

  1. በጨረታው ለመካፈል ተጫራቾች አግባብነት ያለው የዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት(VAT)፣የግብር ከፋይ መለያ የምስክር ወረቀት(TIN)፣የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባወጣው የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀትና ጨረታ ላይ እንዲሳተፉ ከግብርና ታክስ ሰብሳቢ መ/ቤቶች የሚሰጣቸውን የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች ለምድብ አንድ ብር 50,000.00(ሃምሳ ሺህ) እና ለምድብ ሁለት ብር40,000.00(አርባ ሺህ) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) በባንክ ጋራንቲ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ከመጫረቻ ሠነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች የቴክኒክ እና የፋይናንስ የመወዳደሪያ/የመጫረቻ ሰነዶች በታሸጉ ኢንቨሎፖች በአንድ ኦሪጂናልና በአንድ ኮፒ እስከ 13/4/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ድረስ በድርጅቱ የስብሰባ አዳራሽ ቢሮ ቁጥር 602 ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  4. ጨረታው በዚሁ ቀን 13/4/2019 ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ዕለት 4:05 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በቢሮ ቁጥር 602 ይከፈታል።
  5. ተጫራቾች የእያንዳንዱ ምድብ የጨረታው ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን አንስቶ ከድርጅቱ ግዥና ትራንስፖርት ክፍል ቢሮ ቁጥር 011 መውሰድ ይችላሉ።
  6. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- ሜክሲኮ አደባባይ ወደ ሳርቤት በሚወስደው መንገድ 300 ሜትር ዝቅ ብሎ
ስልክ ቁጥር፡- 011-551-32-88
ፖሣቁ 3375 አአ

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት

Summary
Ethiopian Petroleum Supply Enterprise buys children's outdoor playground equipment (Lot 1) and construction materials: cement, rebar, timber, black wire and nails (Lot 2). Licensed, VAT-registered suppliers on the supplier list may bid.
Save Tender Remind me on Telegram
Report a problem with this tender