Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Sugar Industry Group Omo Kuraz No-2 Sugar Factory
  • Address , Phone: 0991149485
  • Website
  • Deadline09 Dec 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document Price500(አምስት መቶ ብር)
  • Bid Securityብር 100,000 CPO
  • opening dateበዚሁ ቀን 8:30 ሰዓት
  • Sector Steel, Metals And Aluminium , Disposal Sale

የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ ከግንባታ የተረፈ 200 ቶን ቁርጥራጭ ብረታ ብረት ለመሸጥ ለሶስተኛ ዙር ያወጣው ብሔራዊ ግልፅ የሽያጭ ጨረታ (ቁጥር አሽጨ 001/ኦኩስፋ/ቁ-2/2018)።

Ethiopian Sugar Industry Group Omo Kuraz No-2 Sugar Factory

Add to calendar Google Calendar Download .ics

ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የሽያጭ ጨረታ ቁጥር- አሽጨ 001 / ኦኩስፋ/ቁ-2/2018(ለሶስተኛ ዙር የወጣ)

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ስኳር ኢዱስትሪ ግሩፕ የኦም ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ ከዚህ በታች የተጠቀሰውን ዕቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ሎት 1፡- ከግንባታ የተራረፉ ቁርጥራጭ ብረታ ብረት 200 ቶን ሽያጭ ጨረታ

ስለዚህ፡-

  1. በዘርፉ የተሰማራችሁና በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ፣ የቫት ምዝገባ ሰርተፊኬት እንዲሁም የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
  2. በጨረታው መከፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የተዘጋጀውን የተሟላ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ዓርብ) ከሰዓት በፊት ከ2:30 - 6:00 ከሰዓት በኋላ ከ7:00-10:30 እና ቅዳሜ ከሰዓት በፊት ከ2:30 - 6:00) ቀጥሎ ከተመለከተው አድራሻ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ/ በባንክ የተመሰከረለት (CPO) ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  5. ተጫራች ለተጫረተው ዕቃ መነሻ ዋጋ መሰረት ለመግዛት በቂ አቅም መኖሩን ለማረጋገጥ የባንክ ስቴትመንት ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  6. ይህ ጨረታ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ክፍት ሆኖ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8:00 ተዘግቶ 8:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል።
  7. ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 60 ቀናት ነው።
  8. የጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ የጨረታው ዋጋ ጸንቶ ከሚቆይበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ለተከታታይ 60 ቀናት ነው።
  9. የዕቃው ርክክብ የሚፈፀመው ኦም ኩራዝ ቁጥር ሁለት ስኳር ፋብሪካ የሚገኝበት ማለትም ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን ኃይል ውሃ ቀበሌ ነው።
  10. ድርጅቱ የተሻ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  11. የጨረታው ሰነድ የሚሸጥበት፣ የሚገባበትና የሚከፈትበት አድራሻ ቀጥሎ የተመለከተው ይሆናል።

አድረሻ ፡- ኦም ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት አዲስ አበባ ነው።
ለበለጠ መረጃ ይንን የስልክ ቁጥር መጠየቅ ይቻላል 0991149485 /0940209464/0986862766

የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ

Summary
Omo Kuraz No. 2 Sugar Factory (Ethiopian Sugar Industry Group) sells 200 tonnes of scrap metal left over from construction, third round. Bidders must show a bank statement proving capacity; delivery is at the factory in South Omo zone.
Save Tender Remind me on Telegram
Report a problem with this tender

የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የባሕር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የተወረሱ አልባሳት፣ ጫማዎች፣ ኮስሞቲክስ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችና ባለ 2 እግር ተ...

READ MORE