Tender Detail

Tender Details

  • Company የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት (FDRE Refugees and Returnees Service)
  • Address የእንቁላል ፋብሪካ አደባባይን ሳይሻገሩ ከፌዴራል ፖሊስ ክበብ ፊት ለፊት : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 813 21 93
  • Websitehttps://rrs.et/
  • Deadline01 Dec 2026, 10:30 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document Price200(ሁለት መቶ ብር)
  • Bid Securityየአጠቃላይ ዋጋ 2% CPO ወይም የባንክ ዋስትና
  • opening dateህዳር 22 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 5:00 ሰዓት
  • Sector Disposal Sale , Used Items

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ያገለገሉ ኤሌክትሮኒክስ፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ የስታፍ ብረቶች፣ ቆርቆሮዎች፣ ጌት ቫልቮች፣ ሚስማሮችና ሌሎች ዕቃዎችን ለመሸጥ ያወጣው ያገለገሉ ዕቃዎች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ።

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት (FDRE Refugees and Returnees Service)

Add to calendar Google Calendar Download .ics

ያገለገሉ ዕቃዎች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት እንቁላል ፋብሪካ አካባቢ በሚገኘው ዋና መስሪያ ቤት ቅጥር ግቢ እና በሚክሲኮ ጋራዥ ውስጥ የሚገኙትን የተለያዩ ዕቃዎች በጅምላ እና በችርቻሮ እንዲሸጡ በተወሰነው መሰረት የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ፣ ያገለገሉ የተሽከርካሪ መለዋወጫ እና የተለያዩ ስታፋ ብረቶች፣ ጌት ቫልቮች፣ ኤልቦዎች፣ የብረት መስኮቶች፣ የኮረንሲስ ቆርቆሮዎች፣ ብረቶች ባለ 8#፣ ጂ ኤ ቢንቢዎች፣ ሚስማሮች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ባወጣው የዕቃዎች ሽያጭ ጨረታ መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች፡-

  1. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የሽያጭ ጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል እንቁላል ፋብሪካ አካባቢ በሚገኘው የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት መ/ቤት ቅጥር ግቢ የፋይናንስ ቢሮ በመገኘት እና ክፍያ በመፈጸም ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ከህዳር 14 ቀን 2019 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ህዳር 22 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30 ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይቻላል።
  2. በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚያቀርቡትን አጠቃላይ ዋጋ 2% ለስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት/Refugees and Returnees Service /በሚል የተዘጋጀ የክፍያ ማዘዣ / CPO/ የባንክ ዋስትና /Bank Gurantee/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  3. ማንኛውም ተጫራች ከህዳር 14 ቀን 2019 ዓ/ም እስከ ህዳር 22 ቀን 2019 ዘወትር በስራ ሰዓት ጉለሌ በሚገኘው የአገልግሎት መስሪያ ቤት ቅጥር ግቢ በመገኘት ዕቃዎቹን መመልከት ይችላል። ቅዳሜና እሁድ የስራ ቀናት አይደሉም።
  4. ጨረታው ጉለሌ እንቁላል ፋብሪካ በሚገኘው የአገልግሎት መስሪያ ቤት ቅጥር ግቢ የሚካሄድ ሲሆን የጨረታው ሳጥን ህዳር 22 ቀን 2019 ከጠዋቱ 4:30 ታሽጎ በዕለቱ ከጠዋቱ 5:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል።
  5. የጨረታ አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ያስያዙት ሲፒኦ ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ዋስትና በ3 ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
  6. ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ወይም በማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃዎችን መረከብ አለባቸው።
  7. በተራ ቁጥር 6 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረገ ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዘው ሲፒኦ ለአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ገቢ በማድረግ የተሻለውን አማራጭ የመውሰድ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  8. አገልግሎት መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  9. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር +251910474668 ወይም 251911569913 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት

Summary
Refugees and Returnees Service (Addis Ababa) sells used items in bulk and retail as-is: electronics, used vehicle spare parts, steel sections, gate valves, elbows, metal windows, corrugated sheets, rebar, GI pipes and nails. Items can be viewed at its Gulele compound.
Save Tender Remind me on Telegram
Report a problem with this tender