Tender Detail

Tender Details


በለሚ ኩራ ክ/ከተማ የቤኬ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የጽህፈት፣ የጽዳት፣ የደንብ ልብስ፣ ቋሚና ልዩ ልዩ እቃዎች፣ ህትመት፣ ትራንስፖርትና የጉልበት ሰራተኛ ግዥ በ8 ሎት ያወጣው ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ (ቁጥር 001/2019)።

በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ቤኬ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት

Add to calendar Google Calendar Download .ics

የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታው መ/ቁጥር 001/2019 ዓ.ም

የቤኬ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2010ዓ.ም ለተለያዩ የስራ ክፍሎች የሚሆኑ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት እቃዎችን አገልግሎቶችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ ለመግዛት ይፈልጋል (ከእያንዳንዱ ሎት ጎን የተቀመጠው የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ነው)፡

  • አላቂ የፅህፈት እቃዎች ሎት 1 --------- 50,000.00
  • የጽዳት እቃዎች ሎት 2---------40,000.00
  • የደንብ ልብስ ሎት3---------35.000.00
  • ቋሚ እቃዎች ሎት4----------60,000.00
  • ልዩ ልዩ እቃዎች ሎት5-------- 30,000.00
  • የህትመት ሥራዎች ሎት 6----- 10,000.00
  • የትራንስፖርት አገልግሎት ሎት 7-------5000 00
  • የጉልበት ሰራተኛ ሎት8-----------------11,000.00

የሚወዳደሩ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች

  1. በዘርፉ የተሰማሩ መሆን አለባቸው
  2. የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
  3. የቫት ተመዝጋቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
  4. በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የሚገኙና ለዚሁም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
  5. የሚቀርበው ዋጋ ቫትን የጨመረ መሆኑን መግለጽ አለባቸው
  6. የጨረታ ሰነዱን በየሎቱ የማይመለስ 500.00 ብር (አምስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ከፋይናንስ ክፍል መውሰድ ይችላሉ
  7. እስፔስፊኬሽን ላልቀረበላቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው።
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በCPO/ ብር ) በየሎቱ በተቀመጠው መሰረት ማስገባት ይገባቸዋል።
  9. የጨረታ ማቅረቢያ ጊዜው ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከ2:30 እስከ 11:30 ሰዓት ድረስ ይሆናል።
  10. ጨረታ የሚከፈተው ጨረታው አየር ላይ ከዋለ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት በት/ቤቱ አዳራሽ ይሆናል።11ኛው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል።
  11. ት/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

በሌ አራብሳ ሳይት 05 እንጀራ ቤት ፊት ለፊት ቤኬ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
ስልክ 0116-12-59-12/0116-12-58-12

ማሳሰቢያ
የጨረታ ሰነዱን ስታስገቡ ሙሉውን ሰነድ ሳይቆራረጥ ኦርጅናሉን እና ኮፒውን በመለየት በሰም በታሸገ 2ኤንቨሎፕ ፖስታ ታሽጎ መግባት አለበት። ከላይ የተጠቀሱት ማስረጃዎች በኮፒው የጨረታ ሰነድ ውስጥ በማካተት ሊቀርቡ ይገባል። ጨረታ ሰነዱን ፋይናንስ ቢሮ ማግኘት ትችላላችሁ።

በለሚ ኩራ/ክ/ከ/ት/ጽ/ቤት ቤኬ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት

Summary
Beke General Secondary School (Lemi Kura, Addis Ababa) buys goods and services in 8 lots: stationery, cleaning items, uniforms, fixed assets, sundry items, printing, transport and casual labour. Licensed, VAT-registered suppliers on the supplier list may bid.
Save Tender Remind me on Telegram
Report a problem with this tender