የኢትዮጵያ ባንኮች ማህበር ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ያገለገሉ የቢሮ ፈርኒቸር፣ ኮምፒዩተር እና ተዛማጅ ዕቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ETHIOPIAN BANKERS ASSOCIATION
ያገለገሉ ንብረቶች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥርኢባማ 001/2019
የኢትዮጵያ ባንኮች ማህበር ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ያገለገሉ የቢሮ ፈርኒቸር፣ ኮምፒዩተር እና ተዛማጅ ዕቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
| ሎት 1. የኮምፒዩተሮች እና የአይቲ እቃዎች: | ኮምፒውተሮች፣ላፕቶፕ ፣ፋክስ፣ፎቶ ኮፒማሽን፣ ዩፒኤስ እና ያገለገሉ ካርትሬጅ። |
| ሎት2. ፈርኒቸር እና የመኪና ባትሪዎች: | የተለያዩ ያገለገሉ ወንበሮች፣ ጠረጴዛዎች፣ መደርደሪያዎች /ቁም ሳጥን/፣ ሶፋ ወንበር የልብስ መስቀያ እና ያገለገሉ የመኪና ባትሪዎች ወዘተ.. |
በጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፣
- የሚሸጡ ዕቃዎች በማህበሩ ዋና መ/ቤት መስቀል አደባባይ አዲስ አበባ ስታዲየም ፊትለፊት የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ምዕራብ አዲስ አበባ አንበሳ ህንጻ 3ኛ ፎቅ ከ ህዳር12/2019- ህዳር21/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት እስከ ቀኑ 9:00 ሰዓት ድረስ መመልከት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000.00 (ሀያ ሺ ብር) ሲ.ፒ.ኦ (CPO)በኢትዮጵያ ባንኮች ማህበር ስም አሰርተው ከጨረታ ሰነድ ጋር በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ከነሙሉ አድራሻ የተጫራቹ ስም፣ፊርማ እና ስልክ ቁጥር በመግለጽ እስከ ህዳር 21/2019 ዓ.ም 9:00 ሰዓት ድረስበአካል በመገኘት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል። ከጨረታው ሳጥን መዝጊያ ሰዓት በኋላ የሚደርሱ የመጫረቻ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
- ጨረታው ህዳር 21/2019 ዓ.ም. ከሰዓት በኋላ 9:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በማህበሩ ዋና መ/ቤት ይከፈታል።
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የጨረታ ሰነድ መግዣ የማይመለስብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) የኢትዮጵያ ባንኮች ማህበር ሒሳብ ቁጥር 01304002416500 አዋሽ ባንክ በማስገባት የባንክ ደረሰኝ በማምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራች በሎት ከተገለጹት እቃዎች በከፊል ወይም በተናጠል መጫረት አይችልም።
- ማህበሩ የጨረታውን አሸናፊዎች ካሳወቀበት ቀን ጀምሮ በአምስት ቀናት ውስጥ ገንዘቡን ሙሉ በሙሉ በመክፈል ንብረቶቹን ማንሳት ይኖርባቸዋል። አሸናፊዉ ተጫራች በተቀመጠዉ የጊዜ ገደብ ከፍሎ ንብረቶቹን ካላነሳ ከጨረታው አሸናፊነት ተሰርዞ ለጨረታው ያስያዘው ገንዘብ ለማህበሩ ገቢ ይሆናል።
- በጨረታው ተሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ (CPO) የጨረታ ግምገማ ውጤት ከተገለፀበኋላ ተመላሽ ይደረጋል።
- ማህበሩ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 251-115-533-874 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የኢትዮጵያ ባንኮች ማህበር
Summary
Ethiopian Bankers Association is selling used computers, IT equipment, office furniture and car batteries as-is by sealed bid in two lots.
