Tender Detail

Tender Details


አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን (ሎት 1) እና የተሽከርካሪ ጎማዎችና ባትሪዎችን (ሎት 2) ለመሸጥ ያወጣው ግልጽ የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ (ቁጥር AAU/NCB/pd/13/2019)።

Addis Ababa University

Add to calendar Google Calendar Download .ics

ግልጽ የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር፡-AAU/NCB/pd/13/2019

ሎት 1፡-ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች፤
ሎት 2፡- የተሽከርካሪ ጎማዎችና ባትሪዎች ሽያጭ ጨረታ

  1. አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከላይ በሎት የተጠቀሱትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
  2. ተሽከርካሪዎቹ የሚገኙበት አድራሻ 6 ኪሎ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢና ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ፋኩልቲ ሞተረፑል ሲሆን ለመግዛት ፍላጎትና ብቃት ያላቸዉ ተጫራቾች በታሸገ ኢንቨሎፕ የጨረታ ሰነድ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እንድታቀርቡ ተጋብዛችኋል።
  3. ጨረታዉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ግዥና ንብረት አስተዳደር መመሪያ ሥነ-ሥርዓት መሰረት ይፈፀማል።
  4. ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ከዚህ በታች በተራ ቁጥር 7 (ሀ/ በተገለፀው አድራሻ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በዩኒቨርሲቲዉ የኢትዮጲያ ንግድ ባንክ አካዉንት ቁጥር 1000087392067 ገቢ በማድረግ ስለእቃዎቹ ሙሉ ዝርዝር የያዘዉን ሰነድ መዉሰድ ይችላሉ።
  5. የጨረታ ሰነዱን ከዚህ በታች በተራ ቁጥር 7 (ለ) በተገለጸዉ አድራሻ እስከ ህዳር 25 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ ጠዋቱ 4:00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ። የጨረታ ማስከበሪያዉ በተጫራቾች መመሪያ በተዘረዘረዉ መሰረት አያይዘዉ ያቀርባሉ። ዘግይተዉ የሚቀርቡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸዉም። ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቁጥር 7 (ሐ) በተጠቀሰዉ አድራሻ ህዳር 25 ቀን 2019 ዓ.ም ጠዋት 4:30 ሰዓት ይከፈታል።
  6. ተጫራቾች ከዚህ በታች በተራ ቁጥር 7 (ለ) በተገለጸዉ አድራሻ ህዳር 25 ቀን 2019 ዓ.ም ጠዋት 4:00 ሰዓት ወይም በፊት በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ የጨረታ ሰነዱን በማስገባት (በግዥ እና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ከጨረታ መክፈቻ ጊዜ በፊት ማቅረብ አለባቸዉ። ተጋባዥ ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ለሎት 1 ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) እንዲሁም ለሎት ሁለት ብር 20,000.00 (ሃያ ሺ ብር) በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ በተጨማሪም ጨረታዉ ከተከፈተ በኋላ ማንኛዉም ተጫራች ከዉድድሩ ከወጣ የተያዘዉ የጨረታ ማስከበሪያ የሚወረስ ይሆናል።
  7. ሀ/ ሰነዶቹ የሚሸጡበት አድራሻ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 307
    ለ/ የጨረታዉ ሰነድ የሚገባበት አድራሻ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 200
    ሐ/ ጨረታዉ የሚከፈትበት አድራሻ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 200
  8. የጨረታ አሸናፊዉ ድርጅት የዉል ስምምነት ከተፈረመበት ቀን በኋላ ባሉት 10 ቀናት ውስጥ ለዩኒቨርስቲዉ ሙሉ ክፍያ በመፈጸም ከከፈለበት ቀን ጀምሮ ባሉት በ10 ተከታታይ ቀናት ውሥጥ እቃዉን ማንሳት አለበት።
  9. ዩኒቨርሲቲዉ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታዉን የመሰረዝ መብት አለዉ።

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

Summary
Addis Ababa University sells used vehicles (Lot 1) and used vehicle tyres and batteries (Lot 2) by sealed bid. Items are at the main campus in Sidist Kilo and the Business and Economics faculty motor pool, Addis Ababa.
Save Tender Remind me on Telegram
Report a problem with this tender