Tender Detail

Tender Details

  • Company Hibret Bank S.C (ሕብረት ባንክ አ.ማ)
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251114655222
  • Websitehttps://www.hibretbank.com.et/
  • Deadline11 Dec 2026, 3:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document Price200(ሁለት መቶ ብር)
  • Bid Securityየመነሻ ዋጋው 1/4 (25%) CPO
  • opening dateታህሳስ 02 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 9:30 ሰዓት
  • Sector Disposal Sale , Used Items

ሕብረት ባንክ አ.ማ ያገለገሉ 5 ተሽከርካሪዎችን (1 ሀዩንዳይ ግራንድ i10 እና 4 ኒሳን ሰኒ) ባሉበት ሁኔታ ለመሸጥ ያወጣው የጨረታ ማስታወቂያ (ቁጥር 006/2019)።

Hibret Bank S.C (ሕብረት ባንክ አ.ማ)

Add to calendar Google Calendar Download .ics

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 006/2019

ሕብረት ባንክ አ.ማ ይጠቀምባቸው የነበሩ ከዚህ በታች የተገለፁትን ብዛታቸው 5 (አምስት) የተለያዩ ዓይነት ተሽከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ተ.ቁየተሽከርካሪው ዓይነትየሠሌዳ ቁጥርየሻንሲ ቁጥርየሞተር ቁጥርየተሽከርካሪው ሞዴልየተሰራበት ዘመንየጨረታ መነሻ ዋጋ
1Hyundai Grand i 103-A1180MALA741CBFM044109G4LA-EM385950I1020142,300,000.00
2Automobile Nissan Sunny3-89252JN1BEAN16Z0001182QG13-392161BDEALHAN16EHAD-B20111,350,000.00
3Automobile Nissan Sunny3-95238JN1BEAN16Z0001319QG13-392307BDEALHFN16EHAD-B20111,400,000.00
4Automobile Nissan Sunny3-79989JN1BEAN16Z0001169QG13-392109BDEALHFN16EHAD-B20111,450,000.00
5Automobile Nissan Sunny3-82445JN1BEAN16Z0001183QG13-392158BDEALHFN16EHAD-B20111,400,000.00

በመሆኑም

  1. ንብረቶቹን ለማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣ ቀን ጀምሮ እስከ ታህሳስ 02 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ ሜክሲኮ ሰንጋ ተራ አካባቢ በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት (ህብር ታወር ሕንፃ) እንዲሁም ሾላ አካባቢ በሚገኘው የባንኩ ሾላ ቅርንጫፍ ግቢ ውስጥ (የሰሌዳ ቁጥሩ 3-A1180 እና 3-89252 የሆኑት ተሽከርካሪዎች ብቻ) ዘወትር ሰኞ፣ ረቡዕ እና አርብ ጠዋት 3:30 እስከ 5:30 እንዲሁም ከሰዓት 8:00 እስከ 10:00 ድረስ በአካል በመገኘት መጎብኘት ይችላሉ።
  2. ማንኛውም ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሉ ለሚፈልገው ተሽከርካሪ የጨረታ መነሻ ዋጋ 1/4 ወይም 25% በሕብረት ባንክ አ.ማ (Hibret Bank S.C) ስም የተሰራ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ) ከጨረታው ሰነድ ጋር በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማስገባት ማቅረብ አለበት።
  3. ተጫራቾች ለዚህ ጨረታ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ/ በአካውንት ቁጥር 1N0403007 አትራቢያቸው በሚገኝ በማንኛውም የሕብረት ባንክ ቅርንጫፍ ገቢ በማድረግ የጨረታ ሰነዱን ከባንኩ ሕብር ታወር ህንጻ 4ኛ ፎቅ መግዛት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ 15% ተ.እ.ታን የሚያካትት ወይም የማያካትት ስለመሆኑ በግልጽ ማስፈር የሚጠበቅባቸው ሲሆን ይህን ሳይገልጹ ቢቀር ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ዋጋ ላይ ባንኩ 15% ተ.እ.ታን በመጨመር የሚያወዳድር ይሆናል።
  5. ጨረታውን ላላሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ/ ሽያጩ ከፀደቀ በኋላ የሚመለስላቸው ሲሆን የጨረታው አሸናፊዎች ደግሞ ያስያዙት ገንዘብ ለሚገዙት ንብረት ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር ይታሰብላቸዋል።
  6. በጨረታው አሸናፊ የሚሆነው ተጫራች በባንኩ የጨረታ አሸናፊ መሆኑ በደብዳቤ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ቀሪውን የሽያጭ ገንዘብ በ10 (አስር) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል የሚጠበቅበት ሲሆን ክፍያውን በተጠቀሰው ቀን ካልፈፀመ ለጨረታ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ (ሲ.ፒ.ኦ) ለባንኩ ገቢ ይሆናል።
  7. ተጫራቾች ንብረቶቹን የሚገዙበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል ሕብር ታወር 4ኛ ፎቅ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ታህሳስ 02 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  8. ጨረታው ታህሳስ 02 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 9:30 ሰዓት በዋናው መስሪያ ቤት 4ኛ ፎቅ በሠራተኞች ካፍቴሪያ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  9. ባንኩ ንብረቶቹን በገዢው ስም ለማዛወር ለሚመለከታቸው መንግስታዊ አካላት ደብዳቤ ይጽፋል።
  10. የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዘ ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች ማለትም ተጨማሪ እሴት ታክስ፣ በሽያጭ እና በሚመለከተው የመንግስት አካል ግምት ምክንያት የሚመጣ የታክስ ልዩነትን፣ ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጪዎች እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ክፍያዎችን ገዥ (የጨረታው አሸናፊ) ይከፍላል።
  11. ባንኩ በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  12. ለበለጠ ማብራሪያ ሕብረት ባንክ ዋና መስሪያ ቤት በስልክ ቁጥር 011 562 10 24 ወይም 0114 16 97 57 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

ሕብረት ባንክ አ.ማ

Summary
Hibret Bank S.C. sells 5 used vehicles as-is by sealed bid: one 2014 Hyundai Grand i10 and four 2011 Nissan Sunny cars. Vehicles can be viewed at its head office (Hibir Tower, Mexico) and its Shola branch in Addis Ababa.
Save Tender Remind me on Telegram
Report a problem with this tender