Tender Detail

Tender Details

  • Company Modjo Customs Branch Office (የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት)
  • Address ሞጆ ፡ ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0222369094
  • Website
  • Deadline28 Nov 2026, 11:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityየሚጫረቱበት ጠቅላላ ዋጋ 5% CPO (ETHIOPIAN CUSTOMS COMMISSION MODJO BRANCH OFFICE)
  • opening dateNot stated in the notice
  • Sector Medical Equipment And Supplies , Sales, Disposals And Foreclosure , Disposal Sale , Cctv Camera

የጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የተተዉና የተወረሱ ሬዚን፣ አልባሳት፣ ሴራሚክ ታይል፣ የህክምና ኤክስሬይ ማሽን፣ የደህንነት ካሜራ፣ ቫልቮች፣ ካስትሮል ዘይትና ሌሎች ዕቃዎችን በአክሽን ኢትዮጵያ ኦንላይን ለመሸጥ ያወጣው ግልፅ ጨረታ (ቁጥር 7-14/2019)።

Modjo Customs Branch Office (የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት)

Add to calendar Google Calendar Download .ics

የተተውና የተወረሱ ዕቃዎች ግልፅ ጨረታ ቁጥር 7-14/2019 ዓ.ም

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አስመጪዎች በተሻሻለው የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 1425/2018 አንቀፅ 3 ንዑስ አንቀፅ 1 መሰረት የተተው ወይም የተወረሱ ዕቃዎችን በአፈ አወጋገድ መመሪያ ቁጥር 167/2012 አንቀፅ 9 መሠረት የተተዉና የተወረሱ ንብረቶችን ማለትም POWDER JACOBI ION EXCHANGE RESINS፣ LADY SKIRT, MEN T-SHIRT, LADY TIGHT AND OTHER CERAMIC TILES ፣ HIGH END MOBILE C-ARM MACHINE & HIGH FREQUENCY DIGITAL X-RAY MACHINE፣ ELECTRIC FIRVRE ADJUSTABLE FLOOR LAMP LIGHT፣ BLINK OUTDOOR 3RD GENERATION WIRELESS SMART SECURITY CAMERA፣ BRASS CHECK VALVE, BRASS FOOT VALVE, BRASS STRAINER FILTER VALVE & OTHERS፣ PVC PLASTIC MOBILE SHELL COVERS FOR SMART PHONE እና CASTROL OIL፣ የተለያዩ አልባሳት፣ ጫማዎች፣ ሽቶዎች፣ ፑርሞዝ፣ ቻርጀር ኬብል እና ሌሎች እቃዎች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በዚህም መሠረት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመሚፈጸምና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

  1. ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር፣ ዓይነት፣ ብዛት፣ የጨረታ ሠነድ እና መመሪያ ከአክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በመግዛት ዕቃዎቹ ከንብረቶቹ ማግለጫ ስር ተያይዞ የሚገኝ ሲሆን አውርደው መመልከት ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች ከአክሽን ኢትዮጵያ ላይ ተመዝግበው የጨረታ ሰነዱን ካገኙ በኋላ ንብረቶችን በአካል ለመመልከት ዘወትር ከሰኞ እስከ ሐሙስ ከጠዋት 2:00 እስከ ቀኑ 6:00 ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7:00 እስከ ቀኑ 10:30 እና ዓርብ ከጠዋት 2:00 እስከ ቀኑ 5:00 ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7:30 እስከ ቀኑ 10:30 እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋት 2:00 እስከ ቀኑ 5:30 መመልከት ይችላሉ።
  2. የጨረታ ሰነዱን ከአክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም /ድረገፅ/ አንላይን ላይ ብቻ መግዛት እና መጫረት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
  3. ተጫራቾች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር በዘርፉ የፀና የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ በአክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ማያያዝ አለባቸው። ሆኖም ግምታዊ ዋጋቸው ከብር 500,000.00 በታች የሆኑ ማናቸውንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሠርተፍኬት ማቅረብ ሳያስፈልግ መወዳደር ይችላሉ።
  4. ማንኛውም ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን የሚጫረትበትን ጠቅላላ ዋጋ 5% ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ጨረታ ከመከፈቱ በፊት በ ETHIOPIAN CUSTOMS COMMISSION MODJO BRANCH OFFICE በሚል ሥም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከአዲስ አበባ፣ አዳማ እና ሞጆ ቅርንጫፎች ብቻ አሰርተዉ አክሽን ኢትዮጵያ ፒደብ. በማስያዝ ወይም በአክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ ባለው የሲፒኦ አማራጮች ኦንላይን ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በመግዛት የሚወዳደሩበትን ዕቃ አስቀድሞ ማየት ያለባቸው ሲሆን ዕቃውን ሳያዩ ለሚያሞሉት ዋጋ ቅ/ጽ/ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም። በጨረታ ተሸጦ የተወሰደ እቃ ተመላሽ አይደረግም፣ ለእቃውም የተከፈለ ገንዘብ አይመለስም።
  6. ተጫራቾች የአክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም (auction.et) ላይ መመዝገብ እና መጫረት ይችላሉ።
  7. የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 8ኛው የሥራ ቀን ጠዋት 5:00 ሰዓት ድረስ በአክሽን ኢትዮጵያ አንላይን ፕላትፎርም መወዳደሪያ ዋጋ ማስገባት ይችላሉ። ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የጨረታውን ሂደትና ውጤት አንላይን መከታተል ይችላሉ።
  8. ተጫራቾች የሚያስገቡት ዋጋ 15% ቫትን ያካተተ መሆን አለበት።
  9. ማንኛውም በግልፅ ጨረታ የሚሳተፍ ተጫራች ጨረታው ከተጀመረ በኋላ ዋጋ መቀየር ወይንም የሌላ ተጫራቾችን ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ አሻሽሎ ማቅረብ አይችልም። በጨረታ ሽያጭ ውድድር ላይ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤት እና ቤተሰብ የሆኑ ሰዎች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም፣ ጨረታው ተጀምሮ ዋጋ ከሰጡ በኋላ እራሱን ከጨረታ ውድድር ማግለል አይቻልም እና የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ግምገማ ተጠናቆ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የጨረታውን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል።
  10. የግልፅ ጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ስለማሸነፋቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ የአሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ አለበት። በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ ገንዘቡ ገቢ ካልተደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል።
  11. በተራ ቁጥር 10 በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ ያሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ አድርጎ ዕቃውን ያላነሳ/ ያልተረከበ እንደሆነ ለሚቆይበት ለተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ ይከፍላል። ሆኖም ዕቃው በ2 (ሁለት) ወራት ውስጥ ካልወጣ እንደተተወ ተቆጥሮ በጨረታ ሽያጭ ይወገዳል።
  12. አሸናፊ ተጫራች ዕቃዎችን ለመረከብና ለማጓጓዝ የሚያስፈልጉ ወጪዎችን ሁሉ ራሱ ይሸፍናል።
  13. ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ለጨረታ የአቀረበውን ዕቃ ብዛት ለመጨመርም ሆነ ለመቀነስ ሙሉ መብት አለው። በጨረታ ተሸጦ በጨረታ አሸናፊው የተወሰደ እቃ አይመለስም።
  14. የአክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በአጭር ስልክ ቁጥር መስመር 9164 ወይም 09-05-11-55-11/011-666-8828 በመደወል ማግኘት ይቻላል።
  15. ለተጨማሪ ማብራሪያ በሥልክ ቁጥር 022-236-90-94 /022-236-01-90-ላይ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

በጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

Summary
Ethiopian Customs Commission, Modjo Branch, auctions abandoned and confiscated goods online via Auction Ethiopia: ion exchange resins, clothing, ceramic tiles, C-arm and digital X-ray machines, security cameras, brass valves, phone covers, Castrol oil, shoes and more.
Not stated in the notice: opening date, bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender Remind me on Telegram
Report a problem with this tender