የኢትዮጵያ ባንኮች ማህበር ያገለገሉ የቢሮ ፈርኒቸር፣ ኮምፒውተሮችና የአይቲ ዕቃዎች እንዲሁም የመኪና ባትሪዎችን በ2 ሎት ለመሸጥ ያወጣው ያገለገሉ ንብረቶች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ (ቁጥር ኢባማ 001/2019)።
ETHIOPIAN BANKERS ASSOCIATION
ያገለገሉ ንብረቶች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ኢባማ 001/2019
የኢትዮጵያ ባንኮች ማህበር ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ያገለገሉ የቢሮ ፈርኒቸር፣ ኮምፒዩተር እና ተዛማጅ ዕቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
| ሎት1. የኮምፒዩተሮች እና አይቲ እቃዎች | ኮምፒውተሮች፣ ላፕቶፕ ፣ፋክስ፣ ፎቶ ኮፒ ማሽን፣ ዩፒኤስ እና ያገለገሉ ካርትሪጅ። |
| ሎት2. ፈርኒቸር እና የመኪና ባትሪዎች | የተለያዩ ያገለገሉ ወንበሮች፣ ጠረጴዛዎች፣ መደርደሪያዎች /ቁም ሳጥን/፣ ሶፋ ወንበር የልብስ መስቀያ እና ያገለገሉ የመኪና ባትሪዎች ወዘተ.. |
በጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-
- የሚሸጡ ዕቃዎች በማህበሩ ዋና መ/ቤት መስቀል አደባባይ አዲስ አበባ ስታዲየም ፊትለፊት የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ምዕራብ አዲስ አበባ አንበሳ ህንጻ 3ኛ ፎቅ ከህዳር 12 ቀን 2019 - ህዳር 21 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት እስከ ቀኑ 9:00 ሰዓት ድረስ መመልከት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000.00 (ሀያ ሺ ብር) ሲ.ፒ.ኦ (CPO) በኢትዮጵያ ባንኮች ማህበር ስም አሰርተው ከጨረታ ሰነድ ጋር በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ከነሙሉ አድራሻ የተጫራቹ ስም፣ ፊርማ እና ስልክ ቁጥር በመግለጽ እስከ ህዳር 21 ቀን 2019 ዓ.ም 9:00 ሰዓት ድረስ በአካል በመገኘት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል። ከጨረታው ሳጥን መዝጊያ ሰዓት በኋላ የሚደርሱ የመጫረቻ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
- ጨረታው ህዳር 21 ቀን 2019 ዓ.ም. ከሰዓት በኋላ 9:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በማህበሩ ዋና መ/ቤት ይከፈታል።
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የጨረታ ሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) የኢትዮጵያ ባንኮች ማህበር ሒሳብ ቁጥር 01304002416500 አዋሽ ባንክ በማስገባት የባንክ ደረሰኝ በማምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራች በሎት ከተገለጹት እቃዎች በከፊል ወይም በተናጠል መጫረት አይቻልም።
- ማህበሩ የጨረታውን አሸናፊዎች ካሳወቀበት ቀን ጀምሮ በአምስት ቀናት ውስጥ ገንዘቡን ሙሉ በሙሉ በመክፈል ንብረቶቹን ማንሳት ይኖርባቸዋል። አሸናፊው ተጫራች በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ከፍሎ ንብረቶቹን ካላነሳ ከጨረታው አሸናፊነት ተሰርዞ ለጨረታው ያስያዘው ገንዘብ ለማህበሩ ገቢ ይሆናል።
- በጨረታው ተሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ (CPO) የጨረታ ግምገማ ውጤት ከተገለፀ በኋላ ተመላሽ ይደረጋል።
- ማህበሩ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 251-115-533 874 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የኢትዮጵያ ባንኮች ማህበር
Summary
Ethiopian Bankers Association sells used items as-is by sealed bid in 2 lots: computers, laptops, fax, photocopier, UPS and cartridges; and office furniture plus used vehicle batteries. Items can be viewed at its head office near Meskel Square, Addis Ababa.
