በጉለሌ ክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ድል በር አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የትምህርት መሳሪያዎች፣ የደንብ ልብስ፣ የፅዳት እቃዎች፣ ኤሌክትሪክ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ መጻሕፍትና የተለያዩ አገልግሎቶች ግዥ በ13 ሎት ያወጣው የጨረታ ማስታወቂያ (ቁጥር 02/2019)።
በጉለሌ ክ/ከተማ ት/ት/ጽ/ቤት ድል በር አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 02/2019
በጉለሌ ክ/ከ ት/ት/ጽ/ቤት ድል በር አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በመደበኛ በጀትና በዉስጥ ገቢ ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ የሚከተሉትን መግዛት ይፈልጋል (ከእያንዳንዱ ሎት ጎን የተቀመጠው የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ነው)፡
- ሎት - 1 ለጽህፈትና የትምህርት መሳሪያዎች - 12,000.00 (አስራ ሁለት ሺህ ብር)
- ሎት - 2 የደንብ ልብስ ግዥ- 17,000.00 (አስራ ሰባት ሺህ ብር)
- ሎት - 3 የፅዳት እቃዎች- 8,000.00 (ስምንት ሺህ ብር)
- ሎት - 4 የኤሌክትሪክና የውሃ እቃዎች - 2,000.00 (ሁለት ሺህ ብር)
- ሎት - 5 ቋሚ ዕቃ ኤሌክትሮኒክስ - 10,000.00 (አስር ሺህ ብር)
- ሎት - 6 የደንብ ልብስ ስፌት አገልግሎት - 1,000.00 (አንድ ሺ ብር)
- ሎት - 7 የት/ቤቱ ክበብ የመምህራን፣ የሰራተኞች እና የተማሪ ክበብ (ካፌ) አገልግሎት- 7000.00 (ሰባት ሺህ ብር)
- ሎት - 8 የተለያዩ ሪፈረንስ የያዙ መፅሐፍቶች - 3,000.00 (ሶስት ሺህ ብር)
- ሎት- 9 የመኪና ትራንስፖርት አገልግሎት- 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር)
- ሎት- 10 የጉልበት እና ጭነት አገልግሎት- 2000.00 (ሁለት ሺህ ብር)
- ሎት- 11 ህትመት- 1,500.00 (አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር)
- ሎት- 12 የፕሪንተርና ማሽነሪ ጥገና አገልግሎት 1,000.00 (አንድ ሺህ ብር)
- ሎት- 13 በረንዳዩ በር፣ መስተወት፣ ኮርኒስ እና ቀለም ቅብ ጥገና አገልግሎት- 2,000.00 (ሁለት ሺህ ብር)
በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ በማስያዝ መሳተፍ የምትችሉ ሲሆን፡-
- በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር የከፈሉ.
- በገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስቴር በአቅራቢነት የተመዘገቡና የምዝገባ ወረቀት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል.
- ተጨማሪ የእሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል.
- የግብር ከፋይነት ምዝገባ ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል.
- በሁለትና ከዛ በላይ ሎት ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ ለእያንዳንዱ ሎት የተሟላ ማስረጃ በማያያዝ በተለያየ ፖስታ በማሸግ መሳተፍ የምትችሉ ሲሆን የተሟላ ማስረጃ የሌለው ሎት ውድቅ ይሆናል.
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት.
- ተጫራቾች ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን ከት/ቤቱ ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 8 በሎት የማይመለስ ብር 200 በመክፈል መውሰድ ትችላላችሁ.
- በመንግስት የተደራጁ ልዩ አስተያየት የሚደረግላቸው ድርጅቶች በድጋፍ ደብዳቤ መሳተፍ የሚችሉት እራሳቸዉ ባመረቱትና እሴት በጨመሩበት እቃዎች ላይ ብቻ ነው.
- ት/ቤቱ ከሚገዛው ዕቃ ግዢ ላይ ከውል በፊት 20% መቀነስ ወይም መጨመር ይችላል.
- አሸናፊው ድርጅት ለውል ማስከበሪያ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ማስያዝ አለበት.
- አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈውን ዕቃ እስከ ት/ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ በራሱ ትራንስፖርት ማድረስ አለበት.
- ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ውስጥ በወሰዱት ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ በሌለበት ሁኔታ ዋጋውን በመሙላት የግዢውን አይነትና የድርጅቱን ሙሉ ማስረጃ የታሸገው ፖስታ ላይ በመጻፍ ኦርጅናልና ኮፒ ፖስታ ላይ የድርጅት ማህተምና ፊርማ በማስቀመጥ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል.
- ለሚያቀርቡት ዕቃዎች ፖስታውን ሲያስገቡ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ናሙናዎች መግባት አለባቸው.
- ትምህርት ቤቱ ካስቀመጠው ተፈላጊነት /specification/ አንሰው ወይም በልጠው የሚመጡ ናሙናዎች ተቀባይነት አይኖራቸውም.
- የትምህርት ቤቱን የጨረታ መመሪያ ከበ ማህተምና ፊርማ በማድረግ ከፖስታው ጋር ማስገባት አለባቸው.
- ጨረታው በ10ኛው ቀን 11:00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በ11ኛው ቀን ጧት 4:00 ሰዓት ላይ ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል.
- ጨረታውን ያሸነፈው ድርጅት ያሸነፈውን ጠቅላላ የዕቃውን መጠን 25% እስከ 6 ወር ድረስ ተጨማሪ ቢጠየቅ በራሱ ዋጋ የሚያቀርብ ይሆናል.
- ትምህርት ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው.
አድራሻ፡- ድልበር አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ከሰሜን ማዘጋጃ ከፍ ብሎ ሴንቴሜሪ ት/ቤት ጎን
ስልክ ቁጥር 011 157 09 42
በጉለሌ ክ/ከ ት/ት/ጽ/ቤት ድል በር አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
Summary
Del Ber General Secondary School (Gulele sub-city, Addis Ababa) buys goods and services in 13 lots: stationery, uniforms, cleaning, electrical and electronics items, reference books, cafeteria, transport, labour, printing and repair services.
