Tender Detail

Tender Details


በአማራ ክልል የደቡብ ወሎ ዞን ለጋምቦ ወረዳ አቀስታ ጠቅላላ ሆስፒታል ለ2019 በጀት ዓመት የጽህፈት፣ የጽዳት፣ የደንብ ልብስ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የመብራት፣ የቧንቧ፣ ህትመት፣ የቢሮ፣ የመኪና ጎማና መለዋወጫ፣ ቋሚ ዕቃዎች፣ መድሃኒትና የህክምና መሳሪያ ግዥ፣ CCTV ካሜራ ገጠማ፣ ጥገናና የመኪና ኪራይ አገልግሎቶችን በግልጽ ጨረታ ለመግዛት ለመጀመሪያ ጊዜ ያወጣው ማስታወቂያ።

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የደቡብ ወሎ ዞን ለጋምቦ ወረዳ አቀስታ ጠቅላላ ሆስፒታል

Add to calendar Google Calendar Download .ics

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን በለጋምቦ ወረዳ ለአቀስታ ጠቅላላ ሆስፒታል የሚውል የጽህፈት እቃ፣ የጽዳት እቃ፣ የደንብ ልብስ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የመብራት እቃ፣ የቧንቧ እቃ የተለያዩ ህትመቶች ቋሚ የቢሮ እቃዎች የመኪና ጎማና የተለያዩ የመኪና መለዋወጫ እቃዎች፣ ቋሚ እቃ /ፈርኒቸር/ የግንባታ እቃ፣ መድሃኒቶች፣ የህክምና መሳሪያዎች እና መለዋወጫዎች፣ CCTV ካሜራ ገጠማ የእጅ ዋጋና ሙሉ ማቴሪያል እና የሰራተኛ የሰዓት መቆጣጠሪያ የጣት አሻራ የሚሰራ የአጥር በር ስራና የግቢ ውስጥ ለውስጥ መንገድ ስራ የላብራቶሪ መሽኖችንና የኤክስሬይ ማሽኖችን ጥገና ሰርቪስ አመታዊ የእጅዋጋ እና የጭነት መኪና ኪራይ ማውረጃና መጫኛን ጨምሮ በ2019 ዓ.ም በጀት አመት 1ኛ ዙር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ በዘርፉ ንግድ ፈቃድ ያለው ማንኛውም ተጫራች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንጋብዛለን።

ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መሳተፍ ትችላላችሁ

  1. በሙያው ዘርፍ (በሚመለከተው በንግድ ስራ) የተሰማሩ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው(ያላቸው)።
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN number) ያላቸው።
  3. የግዥው መጠን 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ) ብርና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸሁን ማስረጃ ፎቶ ኮፒና ኦርጅናል ማህተም በማድረግ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ አለባቸው።
  5. የእቃውን አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔሲፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል
  6. ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች በናሙናው መሰረት ማቅረብ የሚችል/ናሙናውን ከመ/ቤቱ ማግኘት ይችላል።
  7. ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ ከሆኑ በመወዳደሪያ የጨረታ ሰነዱ ላይ ቫትን ጨምራችሁ መሙላት አለባችሁ።
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ የማይመለስ 200ብር (ሁለት መቶ) ብር እየከፈሉ ከደቡብ ወሎ ዞን ከለጋምቦ ወረዳ አቀስታ ከተማ አቀስታ ጠቅላላ ሆ/ል ከዋና ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 41 መግዛት ይችላሉ።
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢል ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (cpo) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (በጥሬ ገንዘብ) ማስያዝ አለባቸው የባንክ ዋስትና ከሆነ ከ90ቀን በታች መሆን የለበትም።
  10. የውል ማስከበሪያ በሚያቀርበው ዋጋ ላይ 10 % ማስያዝ የሚችል።
  11. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወጥ በሆነ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ አቀስታ ጠቅላላ ሆስፒታል ግዥ ኦፊሰር ቢሮ ቁጥር 38 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት አየር) ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 16 ኛው ቀን ድረስ በጥንቃቄ የድርጅቱን ስምና ፊርማ ማህተም በማድረግ እስከ ጠዋቱ 5:00 ሠዓት ድረስ ማስገባት ይቻላል የጨረታ ሳጥኑ 5:15 ላይ ይታሸጋል።
  12. ጨረታው ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) በተገኙበት አቀስታ ጠቅላላ ሆስፒታል ግዥ/ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 38 በ16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 5:30 ላይ ይከፈታል ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታ ራሳቸውን ማግለል አይችሉም።
  13. ጨረታው በሎት (በጥቅል ዋጋ)የሚወዳደር ይሆናል።
  14. እቃው ገቢ የሚሆንበት ቦታ ደቡብ ወሎ ዞን አቀስታ ከተማ አቀስታ ጠቅላላ ሆስፒታል ንብረት ክፍል ነው።
  15. የጨረታ ሰነዱ ስርዝ ድልዝ ካለው ከጨረታ ውጭ ይሆናል።
  16. ተጫራቾች በፖስታው ላይ የሚጫረቱበትን የስራ ዘርፍ መጻፍ ይኖርባቸዋል።

በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ቢፈልግ አቀስታ ጠቅላላ ሆ/ል ቢሮ ቁጥር 36 ድረስ በአካል በመገኘት (በቢሮ በስልክ ቁጥራችን 03 33140366/0927403736/0915541090 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ

ማሳሰቢያ:-

  • ሆ/ሉ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • ተጫራቾች አቤቱታ ካላቸው ውጤቱ በተገለፀ በተከታታይ 5 ቀናት ውስጥ ጨረታውን ላወጣው ግ/ፋ/ን/አስ/የስ/ሂደት በጽሁፍ ማቅረብ አለበት።
  • መድኃኒት የህክምና መሳሪያ ጥገናና ሰርቪስ ሶፍትዌር የመኪና ጭነት ኪራይ ለአንድ አመት የሚቆይ ይሆናል።
  • ሁሉም ጨረታ በሎት/በድምር ዋጋ የሚወዳደር ይሆናል።

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የደቡብ ወሎ ዞን ለጋምቦ ወረዳ አቀስታ ጠቅላላ ሆስፒታል

Summary
Akesta General Hospital (Legambo Woreda, South Wollo, Amhara) buys stationery, cleaning, uniforms, electronics, electrical and plumbing items, printing, furniture, tyres and spares, building materials, medicines and medical equipment, plus CCTV, repairs and truck rental.
Save Tender Remind me on Telegram
Report a problem with this tender

በጉለሌ ክ/ከተማ የሠላም ጤና ጣቢያ የጽህፈት መሳሪያ፣ የጽዳት ዕቃ፣ የደንብ ልብስ፣ የመኪና ዕቃ፣ የኤሌክትሮኒክስ ጥገና፣ የመኪና ኪራይ፣ ህትመት፣ ሪኤጀንትና...

READ MORE
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት ሞራሌ፣ ፕሌይ ውድና የተለያዩ መጠን ያላቸው አጠናዎች ግዥ በ2 ሎት ያወጣው...

READ MORE