Tender Detail

Tender Details

  • Company City Administration of Addis Ababa Construction Design, Building and Consultation Enterprise (የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት)
  • Address አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊት ለፊት የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ቢሮ አጠገብ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 4 62 14 57
  • Websitehttps://addisconstructionwork.gov.et/
  • Deadline01 Dec 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document Price300(ሶስት መቶ ብር)
  • Bid Securityሎት 1 ብር 75,000፣ ሎት 2 ብር 50,000 (CPO ወይም የ90 ቀን የባንክ ዋስትና)
  • opening dateበዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት
  • Sector Wood And Wood Working , Construction Materials And Raw Materials

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት ሞራሌ፣ ፕሌይ ውድና የተለያዩ መጠን ያላቸው አጠናዎች ግዥ በ2 ሎት ያወጣው ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ (ቁጥር የኮ/ዲ/ግ/ማ/ድ/ግ/ጨ/ቁ 12/2019)።

City Administration of Addis Ababa Construction Design, Building and Consultation Enterprise (የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት)

Add to calendar Google Calendar Download .ics

የተለያዩ የእንጨት ግብዓቶች ግዥ ግልጽ ጨረታ

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር የኮ/ ዲ/ግ/ማ/ድ/ግ/ጨ/ቁ 12/2019

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት የሚከተሉትን የእንጨት ግብዓቶች ከዚህ በታች በሎት ተከፍሎ በተቀመጠው መሰረት ከ6 ወር ያላነሰ ጊዜ ውስጥ ውል ፈፅሞ ለማሰራት በግልፅ ጨረታ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል። ሎት 1፡ሞራሌ እና ፕሌይ ውድ (Phywood) ፣ሎት 2፡የተለያዩ መጠን ያላቸው አጠናዎች

በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችል በዘርፉ የተሰጠ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸዉ ማስረጃ ኮፒ አያይዘዉ ማቅረብ የሚችሉ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን ማረጋገጫ ሰርቲፊኬት ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ) ብር በመክፈል በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊት ለፊት የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ቢሮ አጠገብ የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት ቢሮ በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ መግዛት ይችላሉ።

  1. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሎት1፡ 75,000 (ሰባ አምስት ሺህ) ብር ለሎት 2፡ 50,000 (ሀምሳ ሺህ) ብር በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የ90 ቀናት የባንክ ዋስትና (unconditional bid bond guarantee) ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  2. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4:30 ተሳታፊዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
  3. አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈበትን ዕቃ በራሱ የትራንስፖርት ወጭ በድርጅታችን የግንባታ ሳይቶች ወይም ማዕከላዊ መጋዘን ድረስ ማጓጓዝ ይኖርበታል።
  4. የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ግንባታና ማማከር ድርጅት የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊት ለፊት የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ቢሮ አጠገብ ስልክ ቁጥር 0912744923

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት

Summary
Addis Ababa Construction Design, Building and Consulting Enterprise buys timber inputs in 2 lots: morale (timber battens) and plywood, and eucalyptus poles of various sizes, under a contract of at least 6 months. Licensed VAT-registered suppliers may bid.
Save Tender Remind me on Telegram
Report a problem with this tender