Tender Detail

Tender Details

  • Company የድሬዳዋ ምድብ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት ፍትሐብሔር ችሎት
  • Address ድሬዳዋ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: - - - - - -
  • Website
  • Deadline06 Dec 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityየጀነሬተሩን መነሻ ዋጋ 1/4ኛ CPO
  • opening dateህዳር 27 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:10 እስከ 5:10 ሐራጅ ጀነሬተሩ በሚገኝበት ስፍራ
  • Sector Generators , Sales, Disposals And Foreclosure

የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የድሬዳዋ ምድብ 1ኛ ፍትሐብሔር ችሎት በድሬዳዋ ከተማ ቀበሌ 02 በሚገኝ ሆቴል ውስጥ ያለውን 90KVA/72KW የናፍጣ ጀነሬተር ህዳር 27 ቀን 2019 ዓ.ም በሐራጅ ለመሸጥ ያወጣው ማስታወቂያ።

የድሬዳዋ ምድብ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት ፍትሐብሔር ችሎት


የጨረታ ማስታወቂያ

በፍ/ባለመብት አቶ መሳይ ገረመው ብዛኔ እና በፍ/ባለዕዳ ወ/ሮ ብርሃን ከበደ አየለ መካከል ስላለው የአፈፃፀም ክስ ጉዳይ በመዝገብ ቁጥር 101137 የተሰጠውን ውሣኔ ለማስፈፀም በድሬዳዋ ከተማ ቀበሌ 02 እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን አካባቢ በሚገኘው፣ በይዞታ በመል/ሊ 3642 ላይ እየተገነባ ባለው በፍርድ ባለዕዳ ስም በተመዘገበው ሆቴል ውስጥ የሚገኘው /ጀነሬተር/ ወይም 90KVA/72KW የናፍጣ ጀነሬተር በብር 3,500,000.00 (ሶስት ሚሊዮን አምስት መቶ ሺ ብር) መነሻ ዋጋ በጨረታ እንዲሸጥ ታዟል። እንዲሸጥ የታዘዘ በመሆኑ ህዳር 27 ቀን 2019 ዓ.ም በጨረታ አወዳድሮ በሀራጅ መሸጥ አስፈልጓል። ስለሆነም በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 3:00 እስከ 4:00 ድረስ ባለው ጊዜ የተጫራቾች ምዝገባ ጀነሬተሩ በሚገኝበት ስፍራ የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው በተጠቀሰው ቀን እና ጀነሬተሩ በሚገኝበት ስፍራ ከጠዋቱ 4:10 እስከ 5:10 ባለው ጊዜ ይከናወናል። በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ሁሉ ማንነቱን የሚያረጋግጥ መታወቂያ በመያዝ በጨረታው ሊሳተፍ ይችላል። ማንኛውም ተጫራች የጀነሬተሩን መነሻ ዋጋ 1/4ኛ CPO የማስያዝ ግዴታ ይኖርበታል ይህን ሳያያይዝ በጨረታው ላይ አይሳተፍም። ጨረታውን ካላሸነፈ ገንዘቡ ወዲያውን ተመላሽ ይሆንለታል። የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ያሸነፉበትን ገንዘብ 1/4ኛውን ወዲያውኑ በሞዴል 85 በፍ/ቤቱ ፋይናንስ ክፍል ማስያዝ አለባቸው። ቀሪውን 3/4ኛ ገንዘብ ደግሞ ጨረታው በተካሔደ በ15 ቀናት ውስጥ አጠናቀው ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል። ይህንን ማድረግ ካልቻለ ንብረቱ ለ2ኛ የሀራጅ ሽያጭ ሲከናወን ዝቅተኛ ዋጋ ካስመዘገበ ልዩነቱ እና የጨረታውን ወጪ ለመሸፈን የሚገደድ ይሆናል።

የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት የድሬዳዋ ምድብ 1ኛ ፍትሐብሔር ችሎት

Summary
Federal First Instance Court, Dire Dawa Bench, auctions by court order a 90 KVA / 72 KW diesel generator located in a hotel under construction in Kebele 02, Dire Dawa. Anyone with an ID may bid.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender