ኦዳ ኢንተግሬትድ ትራንስፖርት አክስዮን ማህበር ለVOLVO B11R ቪያጎ አውቶቡሶች የተሽከርካሪ መለዋወጫና ጀነሬተር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት በድጋሚ ያወጣው ማስታወቂያ (ቁጥር OIT/N/Bid-02/2019)።
ኦዳ ኢንተግሬትድ ትራንስፖርት አክስዮን ማህበር
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር:OIT/N/Bid-02/2019
ኦዳ ኢንተግሬትድ ትራንስፖርት አክስዮን ማህበር የተሽከርካሪ መለዋወጫ ለተሽ/ ሞዴል-VOLVO Bus- B11R-Via-go/1050/ 2019) ና ጀነሬተር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነድ ገዝታችሁ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳዉቃለን።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትወዳደሩ ተጋብዛችኋል:
- በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያለዉና በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገበ።
- የግብር መለያ ቁጥር(TIN) ያለዉና የቫት(VAT)ተመዝጋቢ የሆነ።
- ለጨረታ ማስከበሪያ ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 1% ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ(CPO/un Conditional Bank Guarante) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ የምችሉ።
- ተጫራቾች የጨረታዉን ዝርዝር መግለጫ ሰነድ ጋዜጣዉ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 14(አሥራ አራት)ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 500(አምስት መቶ) ከፍለዉ ከኦዳ ኢንተግሬትድ ትራንስፖርት ኢማ መከኒሣ በሚገኘዉ ኢሱ-ሳራ ሕንፃ 5ኛ ፎቅ ከግዢ ክፍል መዉሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የዕቃዎቹን የዋጋ ዝርዝር መግለጫ ሰነድ በማዘጋጀት ዋጋዉን ከተጨማሪ እሴት ታክስ(VAT) በመሙላት ስማቸዉን፣ፊርማቸዉንና አድራሻቸዉን በማስፈር ማህተም በማድረግ የጨረታ ዶክመንታቸዉን ኦሪጅናልና ኮፒዉን በተለያየ ካኪ ፖስታ በታሸገ ኤንቬሎፕ በ15ኛዉ ቀን እስከ ጧቱ 4:00 ሰዓት በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታዉ የሚከፈትበት 15ኛዉ ቀን እሁድ ወይም የህዝብ በዓል ቀን ከሆነ ጨረታዉ የሚከፈተዉ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን ይሆናል።
- የጨረታዉ መዝጊያና መክፈቻ በ15ኛዉ ቀን ከጧቱ 4:00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በዚሁ ቀን 4:30 ላይ መከኒሣ በሚገኘዉ በድርጅቱ ዋና መ/ቤት 5ኛ ፎቅ ግዢ ክፍል በይፋ ይከፈታል። ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ባይሳተፉም የጨረታዉን መከፈት አያስተጓጉልም።
- ጨረታዉ ከተከፈተ በኋላ የቀረበዉን የመወዳደሪያ ሀሳብ መቀየር ወይም ማሻሻል ወይም ከጨረታዉ መዉጣት አይቻልም።
- አሸናፊ ተጫራቾች የጨረታዉ ዉጤት ከተነገረበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 የስራ ቀናት ዉስጥ ከዉል ሰጪዉ ጋራ ተስማምቶ መፈረም ይኖርባቸዋል።
- አሸናፊ ተጫራች በሚደረገዉ ዉል መሰረት፣የሚያቀርቡት የተሽከርካሪ መለዋወጫና ጀነሬተር በተጠየቀዉ መሥፈርት በራሱ ትራንስፖርት ገላን በሚገኘዉ በድርጅቱ ነዳጅ ማደያ ዉስጥ ለንብረት ክፍል ገቢ የሚያደርግና የመለዋወጫዎች ብዛት ሊጨመርም ሊቀነስም ይችላል።
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።
ለበለጠ መረጃ: ስልክ ቁጥር 0974320682
ኦዳ ኢንተግሬትድ ትራንስፖርት አማ
Summary
ODAA Integrated Transport S.C. re-tenders the purchase of vehicle spare parts for its Volvo B11R Viago buses and a generator, delivered to its Gelan fuel station. Licensed suppliers on the supplier list with TIN and VAT may bid.
