የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነቀምቴ ዲስትሪክት ቀጥሎ የተመለከቱትን ያገለገሉ ጀነሬተሮችን ባሉበት ሁኔታ በዝግ ሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነቀምቴ ዲስትሪክት
የሐራጅ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነቀምቴ ዲስትሪክት ቀጥሎ የተመለከቱትን ያገለገሉ ጀነሬተሮችን ባሉበት ሁኔታ በዝግ ሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል።
| ተ/ቁ. | ጀነሬተሮቹ አይነት(Types Of Generator) | ሞደል | የሚያመነጩት ኃይል በኪሎ ቮልት አምፒር(KVA) | Tag Number | የሐራጅ መነሻ ዋጋ | በሐራጅ የሚሸጥበት |
| 1 | Kohler | 2019 | 25 | OE-00008722-17 | 162,450 | በዝግ ጨረታ |
| 2 | Visa | 2017 | 30 | OE-00009647-15 | 181,687.5 | " |
| 3 | Welland | 2009 | 45 | OE-00000704-16 | 93,600 | " |
| 4 | Green Power | 2011 | 45 | OE-0000065-13 | 172,800 | " |
| 5 | Ferbo | 2015 | 30 | OE-00000313-09 | 72,525.38 | " |
| 6 | Ferbo | 2015 | 30 | OE-00008721-18 | 96,700.5 | " |
| 7 | Ferbo | 2015 | 30 | OE-00008731-17 | 128,934 | " |
| 8 | Ferbo | 2015 | 45 | OE-00001520-09 | 75,026.25 | " |
| 9 | Ferbo | 2015 | 30 | OE-00008723-17 | 96,700.5 | " |
| 10 | Ferbo | 2015 | 30 | OE-00000137-99 | 128,934 | " |
| 11 | Ferbo | 2015 | 45 | OE-00000310-16 | 200,070 | " |
| 12 | Ferbo | 2015 | 45 | OE-00000650-09 | 250,406 | " |
| 13 | Gazini | ------ | 45 | OE-00000139-99 | 53,772.50 | " |
| 14 | Gazini | ------ | 45 | OE-00008729-17 | 53,772.50 | " |
ማሳሰቢያ
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00/ አንድ መቶ/ በመክፈል ከ ህዳር 07 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነቀምቴ ዲስትሪክት መግዛት ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራች ሌሎች ተጫራቾች በሰጡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይችልም።
- ተጫራቾች የጨረታ መነሻ ዋጋውን 25%/ሃያ አምስት በመቶ/ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ ክፍያ ማዘዣ/CPO/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስም በማሰራት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለንብረቶቹ የሚሰጡት ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ካሰፈሩ በኋላ የጨረታ ማስከበሪያና ሌሎች አስፈላጊ ሰነዶችን በፖስታ በማሸግ ህዳር 23 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 እስከ ቀኑ 10:00 ድረስ ነቀምቴ ዲስትሪክት ጽ/ቤት በመቅረብ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ አስመዝግበው ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ህዳር 24 ቀን 2019 ዓ.ም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት በተራ ቁጥር አራት ላይ በተገለፁት አድራሻዎች ይከፈታል።
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር +251576611014 ነቀምቴ ዲስትሪክት በመደወል እንዲሁም ንብረቶቹ በሚገኙበት የኢ/ያ ንግድ ባንክ ቢፍቱ ነቀምቴ ቅርንጫፍ በግንባር ቀርቦ መጠየቅ ይቻላል።
- ጨረታውን ያሸነፈ አካል፤ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ ንብረቱን በገዛበት ገንዘብ ልክ፤ የVAT፤ ጨምሮ ቀሪ ክፍያ ፈጽሞ ንብረቱን ማንሳት አለበት፤ ንብረቱን በተጠቀሰው ግዜ ውስጥ ካላነሳ፤ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታው ያስያዘው ገንዘብ ገቢ ከተደረገ በኋላ፤በንብረቱ ላይ ሌላ ጨረታ እንዲወጣ ያደርጋል።
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነቀምቴ ዲስትሪክት
Summary
Commercial Bank of Ethiopia Nekemte District is selling used generators of various makes (Kohler, Visa, Welland, Green Power, Ferbo, Gazini) as-is by sealed auction.
