Tender Detail

Tender Details

  • Company በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251112730852
  • Websitehttps://www.fsc.gov.et/
  • Deadline18 Dec 2026, 10:30 AM
  • magazineAddis Zemen
  • CountryEthiopia
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityየመነሻ ግምት 1/4ኛ (CPO፣ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
  • opening dateNot stated in the notice
  • Sector Land , House, Building And Warehouse , Sales, Disposals And Foreclosure

የፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት በቦሌ ክ/ከተማ የሚገኝ መኖሪያ ቤት የሐራጅ ሽያጭ

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት


የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለመብት ወ/ሮ አበበች አድማሱ እና የፍ/ባለዕዳ እነ አቶ ተፈሪ መንክር መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/88423 በታህሳስ 22 ቀን 2013 ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/216221 በህዳር 15 ቀን 2014 ዓ/ም በ03/10/2014 ዓ/ም በ21/2/2016 ዓ/ም በ21/10/2016 ዓ/ም በ19/2/2017 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 2 የሚገኝ የቤት ቁጥር 1107 ስፋቱ 315 ካ/ሜ ላይ ያረፈ ባለአንድ ፎቅ የሆነ መኖርያ ቤት በሰሜን እነ አጥፍወርቅ ኪ/ማርያም ይዞታ፣ በምስራቅ መንገድ ፣በምዕራብ የአጥፍወርቅ ኪ/ማርያም የሀንስ ይዞታ፣ በደቡብ አቶ ይልማ ተክ/ አጠቃላይ ታጥሮ የተያዘው ግቢ ካርታ በአጥፍወርቅ ኪ/ማርያም ቤት የሚያዋስነው መንክር (በአምስት ልጆች) ስም ያለ መሆኑ የካርታ ቁጥር ቦሌ 01/01/3/136-6424/00 የቦታ ስፋቱ 1053 ካ/ሜ ሲሆን አሁን በሐራጁ የሚሸጠው ይዞታ በዚህ ካርታ ውስጥ (ስር) መሆኑ የሚሸጠው ይዞታ እራሱን ችሎ ማህደር የሌለው እና መብት ያልተፈጠረለት ወይም ሰነድ የሌለው የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 4,550,000 (አራት ሚሊዮን አምስት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ታህሳስ 9 ቀን 2019ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 4:30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረበ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል። የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3:30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጎብኘት የሚችሉ ሲሆን፤እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም C.P.O አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።

በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት

Summary
The Federal Courts Judgment Execution Office is auctioning a one-storey residential house in Bole Sub-City, Woreda 2, under a court order. The auction is held at the office auction hall.
Not stated in the notice: opening date, bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender