Tender Detail

Tender Details

  • Company Tsedey Bank S.C. (ፀደይ ባንክ አ.ማ)
  • Address ሰንጋተራ አካባቢ በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት ህንጻ 16ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 09 ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0115584896
  • Websitehttps://tsedeybank-sc.com/
  • Deadline21 Dec 2026, 10:30 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityየመነሻ ዋጋውን ¼ በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲ.ፒ.ኦ በፀደይ ባንክ አ.ማ ስም
  • opening dateታህሳስ 12/2019 ከ4:30 እስከ 6:00 ሰዓት ጨረታ በባንኩ ዋና መ/ቤት 11ኛ ፎቅ
  • Sector Land , House, Building And Warehouse , Business, Industry And Factory Foreclosure

ፀደይ ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 97/90 መሰረት በአዲስ አበባ ቦሌና የካ ክ/ከተሞች የሚገኙ ሁለት B+G+3 መኖሪያ ቤቶችንና በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ የሚገኝ የጅኤፍ የጨው ማቀነባበሪያ ድርጅትን በሐራጅ ለመሸጥ ለሁለተኛ ጊዜ ያወጣው ማስታወቂያ።

Tsedey Bank S.C. (ፀደይ ባንክ አ.ማ)


ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

ፀደይ ባንክ አ.ማ ለአቶ ጌታቸው አባት ለሰጠው ብድር በመያዣ የያዛቸውንና ዝርዝር ሁኔታቸው ከዚህ በታች በሰንጠረዥ የተገለጹትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ተ.ቁየተበዳሪ ስምየንብረት አስያዥ ስምየንብረቱ መገኛ፤ደረጃና ካርታ ቁጥርየጨረታው መነሻ ዋጋ
1አቶ ጌታቸው አባትአቶ ጌታቸው አባትበአ/አ ከተማ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 12 ካርታ ቁጥር ቦሌ 12/40/4/1/20892/10731/01 B+G+3 መኖሪያ ቤት56,013,988.56
2አቶ ጌታቸው አባትወ/ሮ ቤዛ ጌታሁንበአ/አ ከተማ የካ ክ/ከተማ ወረዳ 05 ካርታ ቁጥር የካ/253124/13 B+G+3 መኖሪያ ቤት105,849,696.65
3አቶ ጌታቸው አባትጂኤፍ የጨው ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግ/ማህበርበአፋር ክልል ሰመራ ከተማ የካርታ ቁጥር ሰ/ሎ/ከ/እ/10/9/14 ድርጅት75,348,459.02

በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደምቦች በመገንዘብ ቅድመ ሁኔታዎችን በማሟላት ተጫራቾች እንዲጫረቱ ይጋብዛል።

  1. የቤቱ ጠቅላላ የጨረታ መነሻ ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስን ሳይጨምር የተገለፀ ሲሆን ተጫራቾች የቤቱን የመነሻ ጨረታ ዋጋ ብር ¼ (በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲ.ፒ.ኦ) በፀደይ ባንክ አ.ማ ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  2. የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ የሚረጋገጠዉ የጨረታዉ ዉጤት በሚመለከተው አካል ጸድቆ በባንኩ ደብዳቤ ሲሰጠው ብቻ ይሆናል።
  3. በጨረታው የሚሳተፈው በህግ ሰውነት ያገኘ ከሆነ የድርጅቱ መመስረቻ ጽሁፍ ወይም መተዳደሪያ ደንብ፤ ህጋዊ ሰውነት ያገኘበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት እንዲሁም ህጋዊ ውክልና ማቅረብ አለበት።
  4. በጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈልና በጨረታ ያሸነፈውን ንብረት መረከብ ይኖርበታል። አሸናፊው በ15 ቀናት ውስጥ ገንዘቡን ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል።
  5. በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ጥሬ ገንዘብ ወይም ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል።
  6. የጨረታ አሸናፊው ከሚገዛው ንብረት ዋጋ በተጨማሪ ከቤቱ ጋር የተያያዙ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፡ ግብር፤ ተጨማሪ እሴት ታክስ 15% እና ከስም ዝውውሩ ጋር የሚገናኙ ማንኛውንም ወጭዎች ገዢ ይሸፍናል/ይከፍላል። ዉዝፍ የሊዝ ክፍያ የሚኖር ከሆነ የጨረታ አሸናፊው እንዲሸፍን ጊዜው ላልደረሰ የሊዝ ክፍያም ገዥ ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር እንዲዋዋል ይደረጋል።
  7. ተጫራቾች ቤቱን /ድርጅቱን/ በባንኩ አማካኝነት መጎብኘትና ማየት ይችላሉ።
  8. ጨረታ የሚካሄደው ታህሳስ 12/2019 ከጠዋቱ 3:00 – 4:30 የተጫራቾች ምዝገባ፤ ከ4:30 እስከ ቀኑ 6:00 ሰዓት ጨረታ በአዲስ አበባ ከተማ በልደታ ክ/ከተማ ልዩ ቦታው ሰንጋ ተራ በባንኩ ዋና መ/ቤት 11ኛ ፎቅ ይሆናል።
  9. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ:- ፀደይ ባንክ ዋና መ/ቤት በስ.ቁ +251115582978 ደዉሎ መጠየቅ ይቻላል።

ፀደይ ባንክ አ.ማ

Summary
Tsedey Bank S.C. re-auctions foreclosed collateral under Proclamation 97/90: two B+G+3 residential houses in Bole and Yeka sub-cities, Addis Ababa, and the GF salt processing plant in Semera, Afar. Open to individuals and registered companies.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender