የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ቀጥሎ የተመለከቱትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል።
Commercial Bank of Ethiopia (የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
የሐራጅ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ቀጥሎ የተመለከቱትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል።
| ተ.ቁ | የተበዳሪው ስም | የንብረት አስያዥ ስም | የሰሌዳ ቁጥር | ሞተር ቁጥር | የሻንሲ ቁጥር | የንብረቱ አይነት | የሥሪት ዘመን | የሐራጅ መነሻ ዋጋ (ብር) | ሐራጁ የሚከናወንበት ቀን እና ሰዓት | ምርመራ |
| 1 | አሊያንስ ትራንስፖርት ሰርቪስ አ.ማ | ተበዳሪው | 03-AA-A42664 | ISLE310-3178564892 | LJM6HCGE3GAS04588 | ሰንሎንግ 34 ወንበር የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ | 2016 | 662,480.00 | 23/03/2019 ዓ.ም 3:00-4:00 ጠዋት | ቀረጥ አልተከፈለም |
| 2 | ሳዒድ ዳውድ የሱፍ | ተበዳሪው | 3-16057 ኢት | WD615.47170107017627 | LZZ5BLSF-8HA179106 | ደረቅ ጭነት (ሲኖትራክ ሆዎ) | 2020 | 7,996,800.00 | 23/03/2019 ዓ.ም 4:00-5:00 ጠዋት | ቀረጥ ተከፍሏል |
| 3 | አቶ ናስር ካሊል ሞሐመድ | ተበዳሪው | 02-AA-B76699 | JFC92432. | 1FTEX1EP-1JFC92432 | ፎርድ F150 ኪንግ ካፕ | 2018 | 4,765,200.00 | 23/03/2019 ዓ.ም 5:00-6:00 ጠዋት | ቀረጥ ተከፍሏል |
| ተ.ቁ | የተበዳሪው ስም | የንብረት አስያዥ ስም | አድራሻ | የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ ቁጥር/መለያ | ይዞታው ስፋት ካ.ሜ | የይዞታው አይነት/የሚሰጠው አገልግሎት | የሐራጅ መነሻ ዋጋ (ብር) | ሐራጁ የሚከናወንበት ቀን እና ሰዓት |
| 4 | ሚፍተሀ አረብ | አቶ መሃመድ አብደላ ከድር | በአዲስ አበባ ከተማ፣ ኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 07 | AA000090708180 | 171 | የመኖሪያ ህንጻ | 28,315,474.37 | 08/04/2019 ዓ.ም 3:00-4:00 ጠዋት |
| 5 | ሚፍተሀ አረብ | አቶ መሃመድ አብደላ ከድር | በሻሸመኔ ከተማ፣ አራዳ ክ/ከተማ፣ ቡሪካ ጉዲና ቀበሌ | 14020 | 176.17 | የንግድ ህንጻ | 13,191,511.22 | 08/04/2019 ዓ.ም 4:00-5:00 ጠዋት |
| 6 | ማግኖ ኢንዱስትሪያል ኃ.የተ.የግ.ማህበር | ተበዳሪው | በአዲስ አበባ ከተማ፣ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 12 | AA000070408092 | 1000 | ለኢንዱስትሪ እና ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ግንባታ ያረፈበት ይዞታ | 60,514,883.98 | 08/04/2019 ዓ.ም 5:00-6:00 ጠዋት |
| 7 | ብሩክ ገበየሁ ተሰማ | ተበዳሪው | በአዲስ አበባ ከተማ ለሚ ኩራ ክ/ከ ወረዳ 10 | LMK-LTP-LMK10001968-014865 | 241.50 | ለመኖሪያ አገልግሎት የሚዉል G+2 ይዞታ | 22,550,156.34 | 08/04/2019 ዓ.ም 8:00-9:00 ጠዋት |
| 8 | አሸናፊ ያለ. | ተበዳሪው | ኦሮሚያ ክልል፣ሸገር ከተማ አስተዳደር፣ፉሪ ክ/ከተማ | OR00007186211025 | 278.52 | የመኖሪያ ቤት | 16,275,904.24 | 9/04/2019 ዓ.ም 3:00-4:00 ጠዋት |
| 9 | ምስራቅ መንክር | ተበዳሪው | በኦሮሚያ ክልል፣ሰንዳፋ ከተማ፣ በኬ ወረዳ፣ ቀበሌ 02 | 119/106/2012 | 500 | መኖሪያ ቤት | 4,682,351.88 | 09/04/2019 ዓ.ም 4:00-5:00 ጠዋት |
| 10 | ሂሩት ጥዑመልሳን ካሳ | አቶ ኤፍሬም ፍቅሩ | በአዲስ አበባ ከተማ፣ ጉለሌ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 09 | AA000100900339 | 420 | የመኖሪያ ቤት | 26,872,564.19 | 09/04/2019 ዓ.ም 5:00-6:00 ጠዋት |
| 11 | ተስፋዬ ስብሐቱ ገብረእየሱስ | ተበዳሪው | መቀሌ ከተማ፣ ዓዲ ሓቂ ክ/ከተማ | 9304/04/5441 | 140 | ለ99 ዓመት በሊዝ የተያዘ መኖሪያ ቤት | 4,094,133.45 | 8/04/2019 ዓ.ም 3:00-4:00 ጠዋት |
| 12 | አለፈች ገ/ትንሳዔ | ተበዳሪው | በትግራይ ክልል፣ መቐሌ ከተማ፣ ሰሜን ክ/ከተማ | 1156/01/14533 | 2000 | የፋብሪካ ህንጻ | 17,326,923.31 | 08/04/2019 ዓ.ም 4:00-5:00 ጠዋት |
በመሆኑም:-
- ማንኛውም ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሉ የሐራጁን መነሻ ዋጋ 1/4ኛ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ) በማስያዝ መጫረት ይችላል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲ.ፒ.ኦ ማቅረብ ተመራጭ ነው።
- ከተ.ቁ 1-10 የተዘረዘሩ ንብረቶች ጨረታ የሚከናወነው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲሱ ዋናው መስሪያ ቤት 42ኛ (ወለል) ፎቅ ቢሮ ቁጥር 4203 ሲሆን ከተራ ቁጥር 11-12 የተጠቀሰዉ ንብረት ጨረታ የሚከናወነው መቀሌ ዲስትሪክት ቅጥር ግቢ ዉስጥ ነው።
- የንግድ ማህበርን ወክሎ ለመጫረት የማህበሩን መመስረቻ እና መተዳደሪያ ደንብ የያዘና በማህበሩ ስም ንብረት ለመግዛት ስልጣን ያለው መሆን ያለበት ሲሆን ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ በማቅረብ ይሆናል።
- ከመኖሪያ ቤት ውጪ ለጨረታ የቀረቡ ንብረቶችን በጨረታ አሸንፎ የገዛ ሰዉ በሽያጩ ገንዘብ ላይ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ ይከፍላል።
- የጨረታ አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጪዎች ይከፍላል።
- ንብረቶቹን ለመጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋ/መስሪያ ቤት 42 ፎቅ በአካል በመቅረብ ባንኩ በሚያመቻቸው ፕሮግራም መሰረት መጎብኘት ይቻላል፡
- በጨረታው ከፍተኛ የሆነ የጨረታ ዋጋ የሰጠ ተጫራች በባንኩ የጨረታ አሸናፊነት ደብዳቤ ከደረሰው ቀን ጀምሮ ቀሪ የሽያጩን ገንዘብ በ15 ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ያለበት ሲሆን ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ለሐራጁ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል።
- ንብረቶቹን በጨረታ አሸንፎ የገዛ ግለሰብ/ድርጅት የሽያጭ ገንዘቡን ከፍሎ ባጠናቀቀ በ15 ቀናት ጊዜ ውስጥ ንብረቱን መረከብ ያለበት ሲሆን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ንብረቱን ካልተረከበ በንብረቱ ላይ ለሚደርስ ጉዳት ባንኩ ኃላፊነት አይወስድም። ገዢው በተጠቀሰው ጊዜ ንብረቶቹን ካልተረከበ ከንብረቶቹ ጋር በተያያዘ ለሚኖር ወጪ ኃላፊነቱን ይወስዳል።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር:- 0111-13-05-11 በመደወል ወይም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲሱ ዋና መ/ቤት 42ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው ሕግ ክፍል በአካል ቀርቦ ማነጋገር ይቻላል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
Summary
Commercial Bank of Ethiopia is auctioning collateral: a bus, a Sinotruk truck and a Ford F150, plus residential, commercial, industrial and factory properties in Addis Ababa, Shashemene, Sheger, Sendafa and Mekelle.
Not stated in the notice: opening date, bid document price. Check the original document or ask the issuer.
