Tender Detail

Tender Details

  • Company የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ምርጥ ዘር ድርጅት (ቴፒ)
  • Address , Phone: +251913960522
  • Website
  • Deadline28 Nov 2026, 9:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • CountryEthiopia
  • Bid Document Priceብር 300.00 (የማይመለስ)
  • Bid Securityየጠቅላላ ዋጋ 2% (CPO ወይም የባንክ ጋራንቲ)
  • opening dateበቀን 19/03/2019 ዓ/ም ጠዋት 3:30
  • Sector Sales, Disposals And Foreclosure , Agricultural Products

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ምርጥ ዘር ድርጅት የሰሊጥ ምርት ሽያጭ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ምርጥ ዘር ድርጅት (ቴፒ)


ስሊጥ ለመሸጥ የወጣ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

(የጨረታ ቁጥር ደምኢምዘድ-ጨ01/2019)

በደ/ም/ኢ/ሕ/ክ/መንግሥት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ምርጥ ዘር ድርጅት በ2018 ዓ/ም ምርት ዘመን ያመረተውንና በክልሉ ሸካ ዞን የኪ ወረዳ [...] እርሻ ማሳ የሚገኘውን 55 ኩንታል ሰሊጥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም

  1. ተጫራቾች በዘርፉ ለ2019 ዓ/ም የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ የግብር ከፋይ ሰርተፊኬት(TIN) ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 2% በምርጥ ዘር ድርጅቱ ሥም የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ cpo ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ማስያዝ አለባቸው።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በክልሉ ሸካ ዞን ቴፒ ከተማ ከሚገኘው የድርጅቱ ቢሮ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የሠሊጥ ምርቱ በሚገኝበት በክልሉ ሸካ ዞን የኪ ወረዳ መጋዘን በመገኘት የሰሊጡን ሁኔታ በማየት መጫረት አለባቸው። ነገር ግን ይህ ሳይሆን ቀርቶ ዋጋ ቢያቀርብ ኃላፊነቱ የተጫራቹ ይሆናል።
  5. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ቅጹ የሚጠይቀውን በሙሉ አሟልቶ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  6. ተጫራቾች በሌላኛው ተጫራች ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ አይችሉም።
  7. የሰሊጡ መጠን በጥቂት ኩንታሎች ሊያንስ ይችላል።
  8. ተጫራቾች የቴክኒካል ዶክመንታቸውን (ንግድና ተያያዥ) መረጃዎች ኮፒዎችን በአንድ ፖስታ በማሸግ እንዲሁም ዋጋ የሞሉበትን የጨረታ ሰነድ በሌላ ፖስታ በማሸግ እስከ ሕዳር 19/2019 ዓ/ም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ድረስ ቴፒ በሚገኘው በድርጅቱ ግዥ፣ ሽያጭና ገበያ ማስፋፊያ ክፍል ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀ የጨረታ ሣጥን ማስገባት ይችላሉ።
  9. ጨረታው በዕለቱ ማለትም በቀን 19/03/2019 ዓ/ም ጠዋት 3:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  10. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  11. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251913960522 ደውለው መረዳት ይችላሉ።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ምርጥ ዘር ድርጅት (ቴፒ)

Summary
South West Ethiopia Seed Enterprise (Tepi) is selling sesame produced in the previous season and stored in Yeki woreda, Sheka zone, by open bid. Bidders may inspect the sesame at the warehouse.
Save Tender