Tender Detail

Tender Details


ሲንቄ ባንክ አ.ማ በሐዋሳ ከተማ ታቦር ክ/ከተማ የሚገኝ 200 ካ.ሜ መኖሪያ ቤት በመነሻ ዋጋ ብር 12,337,703.27 እና በምስራቅ ሸዋ ዞን ሉሜ ወረዳ የሚገኝ 40,000 ካ.ሜ የስጋ ማምረቻ መጋዘን በመነሻ ዋጋ ብር 48,217,693.17 በሐራጅ ለመሸጥ ያወጣው ማስታወቂያ (ሲባ/ቺሌኡ/ሐራጅ/07/2019)።

SIINQEE BANK S.C.


የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

ቁጥር ሲባ/ቺሌኡ/ሐራጅ/07/2019

ሲንቄ ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 97/1990(እንደተሻሻለው) በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ቀጥሎ የቀረቡትን ንብረቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ተ.ቁየተበዳሪ ስምየንብረት አስያዥ ስምአበዳሪ ቅርንጫፍለጨረታ የቀረበው ንብረትከተማ/ክ/ከተማ/ቀበሌ/ወረዳ/የቤት ቁጥርየካርታ ቁጥርየቦታ ስፋትየጨረታ መነሻ ዋጋ በብርጨረታው የሚከናወንበት ቀንሰዓትጨረታው የወጣው
1በረከት ወርቁ አደራበረከት ወርቁ አደራአዳመኖሪያ ቤትሲዳማ ክልል ሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ታቦር ክ/ከተማ ፊራ ቀበሌ31849200 ካ.ሜ12,337,703.2714/4/20194:30-6:00ለመጀመሪያ ጊዜ
2አሊ ሐላኬ ቦሩአሊ ሐላኬ ቦሩአዳለስጋ ማምረቻ(Meat processing) የሚውል መጋዘንምስራቅ ሸዋ ዞን ሉሜ ወረዳ ሙዳ ሰንቀሌ ቀበሌ756/1700117/1640,000 ካ.ሜ48,217,693.1712/4/20194:30-6:00ለመጀመሪያ ጊዜ

የሐራጅ ደንቦች፤

  1. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪል የጨረታውን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ (1/4ኛ) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ.) ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ። አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በአሥራ አምስት (15) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል። በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል።
  2. በሐራጅ ሂደት ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበው ተጫራች ማን እንደሆነ ብቻ የሚገለፅ ሲሆን ጨረታውን ያሸነፈው ሰው/አካል ስለማሸነፉ በሚመለከተው የባንኩ አካል ከተረጋገጠ በኋላ ማሸነፉን የሚገልጽ ደብዳቤ ይሰጠዋል።
  3. ላላሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ በዕለቱ ይመለስላቸዋል።
  4. በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ ተበዳሪ እና ንብረት አስያዥ ወይም ሕጋዊ ተወካዮች ብቻ ናቸው።
  5. ሐራጅ የሚካሄድበት ቦታ ተራ ቁጥር 1 ላይ ለሚገኘው ንብረቶቹ የሚገኙበት ቦታ ተራ ቁጥር 2 ላይ ለሚገኝ ንብረት አዳማ ከተማ ሲንቄ ባንክ አዳማ ዲስትሪክት ይሆናል።
  6. በጨረታው ቀን ከ4:30 እስከ 5:00 የተጫራቾች ምዝገባ ሰዓት ሲሆን፣ ከ5:00 ሰዓት በኋላ የተጫራች ምዝገባ አይኖርም። ከ5:00-6:00 ሐራጁ የሚካሄድበት ጊዜ ይሆናል።
  7. ለስም ዝውውር የሚከፈል ክፍያ እንዲሁም የሊዝ እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ከግብር ጋር ተያያዥ የሆኑ ክፍያዎችን ገዢው/አሸናፊው ይከፍላል።
  8. የንግድ ማህበራትን በመወከል መጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብ የማህበሩን ህጋዊ ሰውነት ያለው መሆኑን የሚያረጋግጥ የመመስረቻ ወይም የመተዳደሪያ ደንብ እንዲሁም ህጋዊ የውክልና ስልጣን ሰነድ ይዞ መቅረብ ይጠበቅበታል።
  9. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  10. ለሐራጅ የቀረቡ ንብረቶችን ለመጎብኘት የሚፈልግ ከአበዳሪ ቅርንጫፉ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ መጎብኘት ይቻላል።
  11. ተጫራች የጨረታ አሸናፊ ነው የሚባለው አሸናፊነቱን የሚገልፅ ደብዳቤ በፅሑፍ ሲደርሰው ነው።
  12. ለተጨማሪ መረጃ የሲንቄ ባንክ ህግ አገልግሎት ክፍል ስልክ ቁጥር (+251-11557-6016) ፤ አዳ ቅርንጫፍ (0115571965) ላይ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

ሲንቄ ባንክ አ.ማ

Summary
Siinqee Bank auctions two foreclosed properties: a house on a 200 sq m plot in Tabor Sub-City, Hawassa, and a meat-processing warehouse on a 40,000 sq m plot in Lume Woreda, East Shewa. Open to bidders who deposit the required CPO; visits by appointment.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender