Tender Detail

Tender Details

  • Company TSD Engeenering
  • Address , Phone:
  • Website
  • Deadline28 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document Price500(አምስት መቶ ብር)
  • Bid Securityየሚጫረቱበትን የጠቅላላ ዋጋ 2% CPO በቲ.ኤስ.ዲ ስም
  • opening dateNot stated in the notice
  • Sector Sales, Disposals And Foreclosure , Electrical Materials

ቲ.ኤስ.ዲ ኢንጂነሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ከሲመንስ (SIEMENS) ድርጅት ያስመጣቸውን የተለያዩ የኤሌክትሪክ ዕቃዎችና የስልክ ቁርጥራጮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ያወጣው ማስታወቂያ (ቁጥር 001/2019)።

TSD Engeenering


የኤሌክትሪክ ዕቃዎች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 001/2019

ቲ.ኤስ.ዲ.ኢንጂነሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ከሲመንስ (SIMENS) ድርጅት በተለያየ ጊዜያት ያስመጣቸውን እና የገዛቸውን የተለያዩ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች እና የስልክ ቁርጥራጮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም አካል ከዚህ በታች በተመለከተው የጨረታ መመሪያ መሰረት በጨረታው መሳተፍ ይችላል።

  1. ተጫራቾች ከዚህ በታች በተመለከተው የድርጅቱ ፋይናንስ ቢሮ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታውን ሰነድ በብር 500 (አምስት መቶ) ሳሪስ በሚገኘው የድርጅቱ ቢሮ መግዛት ይችላሉ።
  2. ማንኛውም ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዕቃዎቹ በሚገኙበት ሳሪስ ካዲስኮ ህንፃ ጌም ሆቴል አካባቢ በሚገኘው የድርጅቱ መጋዘን በሜዳ ዘወትር በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 3:00 እስከ 10:00 ሰዓት ድረስ መመልከት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች ሊገዙት የሚፈልጉትን ዕቃ LOT የሚያቀርቡበትን ዋጋ በጨረታው ዶክመንት ውስጥ በተዘጋጀው የመሸጫ ዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ላይ በመሙላት ለእያንዳንዱ LOT በተለያየ እና በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ሳሪስ ካዲስኮ ህንፃ ጌም ሆቴል አከባቢ በሚገኘው የድርጅቱ ግቢ ውስጥ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት።
  5. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት LOT ዕቃ የጨረታ ማስረከቢያ የሚጫረቱበትን የጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ (2%) በቲ.ኤስ.ዲ ስም በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ማዘዣ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ከጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል።
  6. ጨረታው ህዳር 19 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 4:00 ይዘጋል። የጨረታው አሸናፊዎች ዝርዝር ከሶስት የስራ ቀናት በኋላ በድርጅቱ የማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ይለጠፋል። አሸናፊውም ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አስር (10) ቀናት ውስጥ ገንዘቡን ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብና ማንሳት ይኖርበታል። ይህ ካልሆነ ግን ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል።
  7. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ: ሳሪስ ካዲስኮ ህንፃ ጌም ሆቴል አካባቢ
ስልክ: +251 11440 33 55/56
ሞባይል: +251 910 27 44 20
ኢሜይል: tsdengineeringplc@gmail.com
ዌብሳይት: www.tsdethiopia.com

ቲ.ኤስ.ዲ ኢንጂነሪንግ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር

Summary
TSD Engineering PLC sells assorted electrical items imported from Siemens and telephone parts by open tender, lot by lot. Items can be viewed at its warehouse near Gem Hotel, Saris, Addis Ababa. Open to any interested buyer.
Not stated in the notice: opening date. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender