የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት በፍርድ ቤት ትዕዛዝ መሰረት በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 06 የቤት ቁጥር 666 የሚገኝ 472 ካ.ሜ ቤትና ይዞታ ታህሳስ 13 ቀን 2019 ዓ.ም በሐራጅ ለመሸጥ ያወጣው ማስታወቂያ።
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት እነ እንግዳ ወርቅ አባቡ እና የፍ/ባለዕዳ እነ ትዕግስት አበበ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 98075 በ15/11/2017 ዓ.ም እና በኮ/መ/ቁ/103848 በ29/03/2018ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/103848 በ22/11/2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 06 የቤት ቁጥር 666 የካርታ ቁጥር 6/67/370438/01 በአነ አበባ ዘውዴ ደስታ ስም የተመዘገበ የቦታ ስፋት 546 ካ/ሜ ውስጥ መዘዙ ከውርስ ሀብት ውጭ የተባለው ቤት 72 ካ/ሜ ስለሆነ ከጠቅላላ ይዞታው ላይ 472 ካ/ሜ የሚደርስ ሲሆን ይዞታው በፕሮፖርሽን ሆኖ ከመዘዙ (ከውርስ ውጭ) ያለው ቤት 472 ካ/ሜ የሆነ ቤት እና ይዞታ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 11,298,587 (አስራ አንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ ዘጠና ስምንት ሺህ አምስት መቶ ሰማንያ ሰባት) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ታህሳስ 13 ቀን 2019 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 4:30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጅ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3:30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ው አስበልጠም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ጽ/ቤት ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን ፍ/ አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልጻለን።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
