አቢሲንያ ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 97/90 መሰረት በአዳማ፣ በአዲስ አበባ ቦሌ ክ/ከተማና በቢሾፍቱ የሚገኙ የፋብሪካ ህንፃ፣ ሆቴል ህንፃ፣ ሪዞርትና መኖሪያ ቤቶችን ጨምሮ አምስት የመያዣ ንብረቶችን በሐራጅ ለመሸጥ ያወጣው ማስታወቂያ።
Bank of Abyssinia S.C. (አቢሲንያ ባንክ አ.ማ)
ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
አቢሲንያ ባንክ አ.ማ ለሰጠው ብድር በመያዣ የያዛቸውን በሠንጠረዥ የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) መሠረት ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋውን ¼ (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በአቢሲንያ ባንክ ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት/ንብረቶች መረከብ ይኖርበታል። በእነዚህ ቀናት ውስጥ የሚፈለግበትን ክፍያ ከፍሎ ንብረቱን ካልተረከበ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል። በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።
- ተበዳሪው/መያዣ ሰጪው በሐራጁ ቀንና ሰዓት በቦታው መገኘት ይችላሉ። ነገር ግን ባይገኙ ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል።
- የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን ፤ ግብር ፣ በሽያጩ ዋጋ ላይ የሚታሰብ የተጨማሪ እሴት ታክስ 15% እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውም ወጪዎችን ይከፍላል።
- ንብረቶቹን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ መጎብኘት ወይም ማየት ይቻላል።
- በባንኩ የብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መሰረት መስፈርቱን ለሚያሟላ የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢ /አሸናፊ/ ባንኩ ከፊል ብድር ሊያመቻች ይችላል።
- ጨረታው የሚካሄደው አዲስ አበባ ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ለገሀር በሚገኘው የአቢሲንያ ባንክ ዋና መስሪያ ቤት ህንጻ B 4ኛ ፎቅ በሚገኘው የፎርክሎዠርና ዴት ሊቲጌሽን ለጨረታ ባዘጋጀው ክፍል ውስጥ ነው።
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 515 0711 ወይም 011 515 1153 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
| ተ.ቁ | የተበዳሪው ስም | የመያዣ ሰጪው ስም | የንብረቱ አይነትና አገልግሎት | የቦታው አጠቃላይ ስፋት በካሬ ሜትር | የካርታ ቁጥር | ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ | የጨረታ መነሻ ዋጋ በብር | ጨረታው የሚካሄድበት ቀን | የምዝገባ ሰዓት | የጨረታ ሰዓት | ለጨረታ የቀረበበት ጊዜ |
|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|
| 1 | ቦሎ የምግብ ኮምፕሌክስ ኃ/የተ/የግ/ማ | ተበዳሪው | የፋብሪካ ህንጻ | 5,950 ካ.ሜ | 293/99/A | ኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አዳማ ከተማ ቦኩ ሸነን ክ/ከተማ | 76,248,147.93 | ታህሳስ 20 ቀን 2019 ዓ.ም | 4:30-5:30 | 5:30-6:00 | በድጋሚ |
| 2 | ቦሎ የምግብ ኮምፕሌክስ ኃ/የተ/የግ/ማ | ተበዳሪው | ለቅይጥ አገልግሎት የሚውል G+4 ህንጻ | 500 ካ.ሜ | 293/99/B | ኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አዳማ ከተማ ቦኩ ሸነን ክ/ከተማ | 37,686,334.67 | ታህሳስ 20 ቀን 2019 ዓ.ም | 8:00-9:30 | 9:30-10:00 | በድጋሚ |
| 3 | ወ/ሮ ማህሌት ዘገየ ጌታቸው | አቶ ደግሰው እያና ተገኝ | መኖሪያ ቤት | 420 ካ.ሜ | የምስክር ወረቀት ቁጥር ETH0001010000-000043107 የይዞታ ልዩ መለያ ቁጥር AA000060705791 | አዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 7 | 30,122,456.21 | ታህሳስ 21 ቀን 2019 ዓ.ም | 4:30-5:30 | 5:30-6:00 | በድጋሚ |
| 4 | ዋይ.ኤጀ ሶሉሽን ኃ/የተ/የግ/ማ | ሰረኒቲ ሎጅ ኃ/የተ/የግ/ማ | ለሪዞርት አገልግሎት የሚውል | በይዞታ ማረጋገጫ (ካርታ) ላይ 21,845.50 ካ.ሜ ሲሆን በመንገድ ማስፋፊያ ምክንያት ከአጠቃላይ ይዞታው ላይ 3,000.00(ሶስት ሺ) ካ.ሜ ተቀንሷል | BI/1401/04 | ቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ቀበሌ 05 | 75,324,695.75 | ታህሳስ 21 ቀን 2019 ዓ.ም | 8:00-9:30 | 9:30-10:00 | በድጋሚ |
| 5 | የ-ኢዝ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ ማህበር | ኢ/ር ኢዛና ኃይለማርያም ብስራት | B+2 የሆነ መኖሪያ ቤት | 278.00 | የምስክር ወረቀት ቁጥር ETH0001000000-00004243794 የይዞታ ልዩ መለያ ቁጥር AA000060301917 | አ/አበባ ከተማ፣ ቦሌ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 3 | 37,119,385.24 | ታህሳስ 22 ቀን 2019 ዓ.ም | 4:30-5:30 | 5:30-6:00 | ለመጀመሪያ ጊዜ |
አቢሲንያ ባንክ አ.ማ
Summary
Bank of Abyssinia auctions five foreclosed properties under Proclamation 97/90: a factory building and a G+4 building in Adama, two residential houses in Bole sub-city, Addis Ababa, and a resort property in Bishoftu. Open to the public; partial bank loans may be offered.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
