Tender Detail

Tender Details

  • Company በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251112730852
  • Websitehttps://www.fsc.gov.et/
  • Deadline21 Dec 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityየንብረቱን መነሻ ግምት 1/4ኛ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO
  • opening dateምዝገባው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ሐራጁ ይካሄዳል
  • Sector Land , House, Building And Warehouse , Sales, Disposals And Foreclosure

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት በፍርድ ቤት ትዕዛዝ መሰረት በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 12 እና በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 10 የሚገኙ ሁለት የመኖሪያ ቤቶችን ታህሳስ 12 ቀን 2019 ዓ.ም በሐራጅ ለመሸጥ ያወጣው ማስታወቂያ።

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት


የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለመብት እነ ጌታቸው ፈረደ እና የፍ/ባለዕዳ እነ ወ/ሮ ሃዳስ ወ/ገብርኤል መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 134514 በ23/7/2014 ዓ/ም እና የፌ/መ/ደ/141112 በ05/11/2014ዓ.ም እና በኮ/መ/ቁ 169625 በጥቅምት 18 ቀን 2018ዓ/ም የፌ/መ/ደ/በኮ/መ/ቁ/172558 በ11/03/2018ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት:

1ኛ በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 12 የቤት ቁጥር ቢ175/10 የቦታ ስፋት 98.06ካ/ሜ የካርታ ቁጥር AA00005120731617501010 የሆነ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 3,222,190.88 ( ሶስት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሃያ ሁለት ሺህ አንድ መቶ ዘጠና ብር ከ88/100) ሆኖ የትራክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ታህሳስ 12 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 4:00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

2ኛ በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 10 የቤት ቁጥር ቢ.40-2-3 ብሎክ 40 የካርታ ቁጥር 10/62/4/11/47846/00 የተመዘገበ የቦታ ስፋት 90ካሜ የሆነ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 6,946,020 (ስድስት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ አርባ ስድስት ሺህ ሃያ ብር) ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ታህሳስ 12 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 4:30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

የሐራጅ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጣቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3:30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመሄድ ለመጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛው አስበልጠም ሆነ አሳንሶ የሚያመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ጽ/ቤት ስም CPO በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት

Summary
The Federal Courts Judgment Execution Office auctions, by court order, two residential houses in Addis Ababa: a 98 sq m plot in Yeka sub-city Woreda 12 and a 90 sq m plot in Lemi Kura sub-city Woreda 10. The buyer pays transaction tax. Open to the public.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender