Tender Detail

Tender Details


የዲላ ፖሊ. ቴክኒክ ኮሌጅ በ2019 ዓ/ም የበጀት ዘመን ለትምህርት ስልጠና የሚውሉ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

Dilla Polytechnic College (ዲላ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ)


የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2019

የዲላ ፖሊ. ቴክኒክ ኮሌጅ በ2019 ዓ/ም የበጀት ዘመን ለትምህርት ስልጠና የሚውሉ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም ዕቃዎች የሚገዛላቸው የትምህርት ክፍሎች

  1. ኢንፎርመሽን ቴክኖሎጅ ዲ/ት
  2. ኤሌክትሪካል ኤሌክትሮንግስ ዲ/ት
  3. አኒማል ፕሮዳክሽን ዕቃዎች
  4. ሆቴል ዲቢት ዕቃዎች
  5. ጋርመንት ዲ/ት ዕቃዎች
  6. የጸጉር ሥራ ዲፓርትመንት ዕቃዎች
  7. የህጻናት ማቆያ ዕቃዎች
  8. ለጋራ አገልግሎት የሚውሉ የደንብ ልብሶች
  9. የመኪና መለዋወጫዎች እና ጎማዎች
  10. የጽዳት ዕቃዎች እና መጋረጃዎች

በመሆኑም ከላይ ለተዘረዘሩ የሥልጠና ዘርፎች እና ሌሎችም ዕቃዎች ለመወዳደር የምትፈልጉተወዳዳሪዎች /አቅራቢዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

  1. ጨረታውን ተወዳደሪ/አቅራቢ/ድርጅት የ2019 ዓ/ም የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል መሆን ይጠበቅበታል ።
  2. የገንዘብና ኢ.ኮ/ል/ሚኒስተር ባዘጋጀው የዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
  3. ተጫራቾች የተጨማሪ እስት ታክስ /ቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው
  4. ተጫራቾች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ የሚችሉና ቋሚ ዕቃዎችን ገዥው መ/ቤት በአካል ቀርቦ ለማየት ከፈለገ ለመተባበር ፍቃደኛ ሊሆኑ የሚችሉ መሆን አለባቸው
  5. ተጫራቾች የዋጋ ዝርዝራቸውን በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ ብቻ ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  6. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ዕቃ ዋጋው ከቫት ውጭና ከነቫቱ በፊት ተብሎ በጥራት መሞላት ይኖርበታል። እንዲሁም ቫት ከተካተተበት ተካቶበታል ተብሎ እንዲሁም ያልተካተተ ከሆነ አልተካተተም ተብሎ ሊጻፍ ይገባዋል ይህ ሳይሆን ቢቀር ቫት እንደተካተተ አድርጎ መ/ቤቱ የሚወስድ መሆኑንእናሳውቃለን ።
  7. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የጠቅላላ ዋጋ 2 % ብር 10,000.00 የጨረታ ማስከበሪያውን በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማስገባት አለበት።
  8. ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ከፖሊ. ኮሌጁ ጋር ውል ተዋውሎ የውል ማስከበርያ የጠቅላላ ዋጋውን 10% ማስያዝ ይኖርበታል። በተጨማሪ ያሸነፈበትን ዕቃ በ15 ቀናት ውስጥ ለኮሌጁ የማቅረብ ግዴታ አለበት።ይህ ሳይሆን ቢቀር ለጨረታ ማስከበርያ ያስያዙት 10 % ገንዘብ በቀጥታ ለፖሊ. ኮሌጁ ገቢ ሆኖከጨረታው የሚሰረዙ ይሆናል።
  9. የጨረታ ሰነዱን ጨረታው ከወጣበት ዕለት አንስቶ ተከታታይ ባሉት 15 ቀናት ከኮሌጁ ግዥና ንብረት አስተዳደር ብሮ ቁጥር 4 በመቅረብ የማይመለስ ብር 500.00/አምስት መቶ/ብር በኮሌጁ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአካውንት ቁጥር GOV 1000019294718 በማስገባትና አድቫይስ በማቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይጠበቅበታል ።
  10. ተጫራቾች የሚቀርቡትን የመወዳደርያ ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ለየብቻ ማህተም አሳርፎበት በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ማቅረብ ይጠበቅበታል።
  11. ጨረታው በ16 ቀን ከጠዋቱ 3.30 ታሽጎ ከጠዋቱ 4.00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል። በተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባለመገኘታቸው የጨረታውን አከፋፈት አያስተጓጉለውም።
  12. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0463312719 ወይም 0463313848 ይደውሉ።

የዲላ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

✨ messages.ai_summary
Dilla Polytechnic College seeks suppliers of training materials for its IT, electrical, animal production, hotel, garment, hairdressing and childcare departments, plus uniforms, vehicle parts, tyres, cleaning items and curtains.
Save Tender