ቦሌ ማተሚያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተለያዩ የሰራተኛ የደንብ ልብስ /ዩኒፎርም/ ማለትም የቆዳ ጫማ፣ የሴፍቲ ቆዳ ጫማ፣ የፖሊስተር ጨርቅ ሆኖ ሰማያዊ ከለር ቱታና ገዋን፣ ሸሚዝ፣ 1ኛ ደረጃ ቴትረን ጨርቅ ሆኖ ኮትና ሱሪ፣ ሱሪ፣ ቀሚስ፣ ከረቫት፣ ኮፊያና የመሳሰሉትን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት/ ማሰፋት/ ይፈልጋል።
ቦሌ ማተሚያ ኃ.የተ.የግ.ማህበር
የሀገር ውስጥ ግዢ ጨረታ ማስታወቂያ
ቦሌ ማተሚያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተለያዩ የሰራተኛ የደንብ ልብስ /ዩኒፎርም/ ማለትም የቆዳ ጫማ፣ የሴፍቲ ቆዳ ጫማ፣ የፖሊስተር ጨርቅ ሆኖ ሰማያዊ ከለር ቱታና ገዋን፣ ሸሚዝ፣ 1ኛ ደረጃ ቴትረን ጨርቅ ሆኖ ኮትና ሱሪ፣ ሱሪ፣ ቀሚስ፣ ከረቫት፣ ኮፊያና የመሳሰሉትን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት/ ማሰፋት/ ይፈልጋል።
- ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የቫት ተመዝጋቢ የምስክር ወረቀት፣ የንግድ ሰርቲፊኬት እና ሌሎችም የህጋዊነት ማረጋገጫ ሰነዶችን ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በቅድሚያ የማይመለስ ብር 400.00 /አራት መቶ/ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 101 በመክፈል ለዚሁ ጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቦሌ መንገድ ከቶታል ነዳጅ ማደያ ዝቅ ብሎ በሚገኘው ቢሮአችን መግዛት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የዋጋቸውን 2% በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /ሲፒኦ/ የባንክ ዋስትና በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ቴክኒካልና ፋይናንሺያል ሰነዶችን በአንድ ፖስታ አሽገው ማቅረብ ይችላሉ። እንደዚሁም ለሚሳተፉበት የአልባሳት አይነት ለጥራት ሙከራ የሚሆን ናሙና አስቀድሞ ወይም ጨረታው በሚከፈትበት እለት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ድረስ በድርጅቱ የግዥ ክፍል ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በ15ኛ የስራ ቀን ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ እለት በ3:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የስብሰባ አዳራሽ ወይም በግዥ ክፍል ይከፈታል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ናሙና የጥራት ደረጃውን የጠበቀ ካልሆነ በዋጋ ዝቅተኛ ቢሆንም እንኳን በጥራት ምዘና የሚሰረዝ ይሆናል።
- በአልባሳት ላይ የሚሳተፍ እና አሸናፊ የሆነ ተጫራች ጨርቅ ከራሱ ሆኖ ከማህበሩ ቢሮ በመምጣትና የሰራተኞቹን ልኬት በመውሰድ በትክክል ሰፍቶ የማስረከብ ኃላፊነት አለበት።
- በአልባሳት ላይ ተሳትፎ አሸናፊ የሆነ ተጫራች ስለስፌቱ አይነት፣ ጥራትና የማስረከቢያ ጊዜና የክፍያ ሁኔታ አስቀድሞ ውል መፈረም ይኖርበታል።
- ድርጅቱ ሌላ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ:-
ቦሌ ማተሚያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
ስልክ ቁጥር:- 0115 15 50 05/0115 51 88 72
ፋክስ:- 0115 51 86 96
ቦሌ ማተሚያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
Summary
Bole Printing PLC seeks suppliers for staff uniforms including leather and safety shoes, overalls and gowns, shirts, suits, trousers, skirts, ties and caps, with tailoring. Samples required.
