የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳደር ጽ/ቤት የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ህትመቶች፣ የጽህፈትና የጽዳት ዕቃዎች ግዥ
የደቡብ ምዕራብ ኢ/ሕ/ክ/መ ርዕሰ መስተዳደር ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳደር ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ተጫራቾች በመጋበዝ እንደሚከተለው በሎት በመከፋፈል ለመግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1. ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች-ኮምፒዉተሮች፣ ፕሪንተሮች፣ ስማርት ሞባይል ቀፎዎች ግዥ
- ሎት 2. የተለያዩ ህትመቶችን
- ሎት 3. የጽህፈት መሳሪያ
- ሎት 4. የጽዳት ዕቃዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች :-
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ ፣ የአቅራቢነት ሰርተፊኬት ፣ የቲን/TIN/ እና የቫት ተመዝጋቢነት ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሱትን መረጃዎች የጨረታ ዶክመንት ሲገዙ ሲመጡ ኦርጅናሉን እና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ አቅርበው እንዲመሳከር የማድረግ ግዴታ አለባቸው።
- በመሆኑም ተጫራቾች የማይመለስ 200/ሁለት መቶ ብር/ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳደር ጽ/ቤት የንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000453947525 ገቢ በማድረግ ስሊፑን በመያዝ ዘወትር በሥራ ሰዓት ለተከታታይ 15 ቀናት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳደር ጽ/ቤት ግዥ ፋይናንስ /ንብ/አስ/ር ዳይሬክቶሬት በመቅረብ ሰነዱን መዉሰድ ይችላሉ።
❖ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ
- ሎት 1ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ኮምፒዉተሮች ፕሪንተሮች ስማርት ሞባይል ግዥ 30,000/ ሰላሳ ሺህ ብር/
- ሎት 2የተለያዩ ህትመቶችን 5,000/አምስት ሺህ ብር/
- ሎት 3.የጽህፈት መሳሪያ 10,000 /አስር ሺህ ብር/
- ሎት4.የጽዳት ዕቃዎችን 5,000/አምስት ሺህ ብር/ደ/ም/ኢ/ሕ/ክ/መ ርዕሰ መስ/ደር ጽ/ቤት ስም በማሰራት ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። የጨረታ ማስከበሪያ በደብዳቤ እንደተገለፀ ለተሸናፊ የሚመለስ ሲሆን ለአሸናፊ ድርጅት የዉል ማስከበሪያ 10% ካስያዘ በኋላ የሆናል።
❖ ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ የሎት ቁጥሩን ሁሉም ፖስታ ላይ በመጻፍ በሰም/በመ/ በታሸገ ኢንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ተከታታይ ቀናት የደ/ም/ኢ/ሕ/ክ/መ ርዕሰ መስ/ደር ጽ/ቤት ግዥ ፋ/ንብ/አስ/ር ዳይሬክቶሬት በመቅረብ ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይችላሉ።
❖ የጨረታው ሳጥን በ16ኛው ቀን በጧቱ 3:30 ሰዓት ታሽጎ በዚያዉ ዕለት ከጧቱ 4:00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊመንግስት ርዕሰመስተዳደርጽ/ቤት ግዥ ፋይናንስን/አስ/ር ዳይሬክቶሬትይከፈታል።
❖ የጨረታ መዝጊያ እና መከፈቻ ቀን ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል። በመከፈቻዉ ዕለት የተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮች ያለመገኘት የጨረታ መክፈት ሂደት አያስተጓጉልም።
❖ አሸናፊዉ ድርጅት ከላይ በሎት የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በሙሉ በራሱ ወጪ ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት መንግስት ርዕሰ መስተዳደር ጽ/ቤት ግዥ ፋይናንስ ንብ/አስ/ር ዳይሬክቶሬት ቦንጋ አቅርቦ የማስረከብ ግዴታ አለበት።
❖ ሎት-3 እና ሎት-4 ተራቾች በስፔኩ የተቀመጡትን ዕቃዎች ናሙና የማቅረብ ግዴታ አለባቸዉ. ናሙና ያላቀረበ ተጫራች ፋይናንሻል አይታይለትም።
❖ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 047 331 1849 በመደወል መጠየቅ ይቻላል!
