በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ ዞን ገሱባ ከተማ አስ/ር ፋ/ፕላን ልማት ዩኒት ለ2019 በጀት ዓመት ለሴክተር መ/ቤቶች አላቂ ዕቃዎች፣ ተሽከርካሪ ወይም ሞተር ሳይክል፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የደንብ ልብስና የህንፃ መሳሪያዎችን በ5 ሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ያወጣው ማስታወቂያ።
በደ/ኢት/ክ/መ/በወላይታ ዞን ገሱባ ከተማ አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ኢ/ህ/ክ/መንግስት በወላይታ ዞን ገሱባ ከተማ አስ/ር ፋ/ፕላን ልማት ዩኒት በ2019 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ለሴክተር መ/ቤቶች ሥራ ጉዳይ የሚውል የተለያዩ ዓይነትና መጠን ያላቸውን ዕቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለምንፈልግ ከዚህ በታች በተዘረዘሩ ሎቶች መወዳደር ይችላሉ።
- ሎት 1 አላቂና ሌሎች አላቂ ዕቃዎች
- ሎት 2 ተሽከርካሪ ወይም ሞተር ሳይክል
- ሎት 3 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
- ሎት 4 የአስተዳደር ሠራተኞች ደንብ ልብስ
- ሎት 5 የህንፃ መሳሪያዎች
ከላይ በተጠቀሱ ሎቶች መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።
የተጫራቾች መመሪያ:-
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ቲን ካርድ፣የንግድ ም/ም/ወረቀት፣አቅራቢነት ም/ም/ወረቀት፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ ሴርቲፊኬት ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሠነድ ኦሪጅናልና ሁለት የኦሪጅናል ኮፒ ለየብቻ በማሸግ የድርጅቱን ሙሉ ስም፣ አድራሻ፣ፊርማ፣የሚወዳደሩበት ሎት እና የድርጅቱ ማህተም በትክክል ተደርጎ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን መክተት ይኖርበታል።
- ፖስታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቹ ራሱን ከጨረታ ማግለል አይችልም።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 10,000 /አስር ሺህ /ብር በጥሬ ገንዘብ ወይም በCPO ማስያዝ ይኖርበታል።
- የጨረታ ሳጥን ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ 15ኛው ተከታታይ የሥራ ቀናት ቀጥሎ በሚውለው የሥራ ቀን 4:00 ታሽጎ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4:30 በገሱባ ከተማ አስ/ር ፋ/ፕላን ልማት ዩኒት ግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ ይከፈታል። ዕለቱ ሰንበት /በዓል/ ከሆነ በቀጣይ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሠዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሠዓት ይከፈታል። ነገር ግን ተጫራቾች በገዛ ፈቃዳቸው በጨረታ ቦታ ያለመገኘት የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም።
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ ላይ የማይነበብና ስሪዝ ድልዝ ያለው መሆን የለበትም።
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከገሱባ ከተማ አስ/ር ፋ/ፕላን ልማት ዩኒት ግዥ ቢሮ በመቅረብ የማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ/ ብቻ በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
- ለአሸናፊው ተጫራች በደብዳቤ ከተገለፀ በሶስት ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ ዋስትና ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% ብቻ በማቅረብ ውል መዋዋል ይጠበቅበታል።
- የጨረታ ማስከበሪያ አሸናፊ ተጫራች እንደታወቀና ውል ከተፈራረመ በኋላ ለተሸናፊ ተጫራቾች ተመላሽ ይደረጋል።
- አሸናፊ ተጫራች ዕቃውን እስከ ገሱባ ከተማ አስ/ር ፋ/ፕላን ልማት ዩኒት ግቢ አድርሶ ያስረክባል።
- መ/ቤቱ የተሻለ ዜዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ:- በሲልክ ቁጥር 0935448792/0913950407 ደውለው ማነጋገር ይችላሉ።
አድራሻ:- ገሱባ ከተማ አስ/ር ፋ/ፕላን ልማት ዩኒት
በደ/ኢት/ያ ክልል/መ/በወላይታ ዞን ገሱባ ከተማ አስ/ር ፋ/ፕላን ልማት ዩኒት
✨ messages.ai_summary
Gesuba Town Finance and Plan Development Unit (Wolaita Zone) buys in 5 lots for sector offices: consumables, a vehicle or motorcycle, electronics, staff uniforms and building materials. Bidders need a renewed licence, TIN, supplier registration and VAT.
