Tender Detail

Tender Details

  • Company የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለስልጣን
  • Address ወልቂጤ ከተማ ወደ ወልቂጤ ኢንዲስትሪያል ኮሌጅ በሚወስደው አስፋልት መንገድ ላይ የድሮው የወልቂጤ ከተማ ስፖርተኞች ማደርያ ጊቢ ውስጥ : በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት : ኢትዮጵያ, Phone: 011 365 9932
  • Website
  • Deadline27 Nov 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document Price300(ሦስት መቶ ብር) ለእያንዳንዱ ሎት
  • Bid Securityብር 150,000.00 በየሎቱ፤ በባንክ ዋስትና ወይም ሲ.ፒ.ኦ (ኢንሹራንስ ተቀባይነት የለውም)
  • opening dateበዚያኑ ከቀኑ 8:30 ይከፈታል።
  • Sector Computer Laptop And Accessories , Electronics Materials

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለስልጣን ለ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የቋሚ ኤሌክትሮኒክስ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ያወጣው ማስታወቂያ (ቁጥር ማ/ኢ/ባ/ኤ/01/19)።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለስልጣን


የጨረታ ማስታወቅያ

የጨረታ ቁጥር ማ/ኢ/ባ/ኤ/ 01/19

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለስልጣን በ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት ላይ የሚውሉ የቋሚ ኤሌክትሮኒክስ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም:-

  1. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችለውን የዘመኑን ግብር የተከፈለበትን ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር የተዛመደ የንግድ ሥራ ወይም የአገልግሎት ሥራ ፈቃድ፣ የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት መንግስት መ/ቤቶች በሚያወጡት ጨረታ ላይ መሳተፍ የሚያስችል የምስክር ወረቀት የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡
  2. ተጫራቾች በታሸገ ኢንቨሎፕ የፋይናንሻል ዋና እና ሁለት ኮፒ የቴክኒካል ፕሮፖዛሉን ዋና እና ሁለት ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማድረግ ኦሪጅናል እና ኮፒ 1፣ ኮፒ 2 በማለት እና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በተለየ ፖስታ ለብቻው በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናቸውን በየሎቱ በተለየ ፖስታ ለብቻው በማሸግ ብር 150,000.00/ አንድ መቶ አምሳ ብር/ ብቻ በቅድመ ሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም ሲ.ፒ.ኦ /c.p.o ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። በኢንሹራንስ ዋስትና የሚቀርብ - የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም።
  4. ተጫራቾች ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00/ሦስት መቶ ብር ብቻ/ ለእያንዳንዱ ሎት በመክፈል ከባለስልጣኑ ዋና መ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኬዝ ቲም ቢሮ በሥራ ሰዓት በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
  5. የጨረታው አሸናፊ የሚወሰነው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች መሰረት ሲሆን ጨረታው ዜግነትን ሳይመለከት ለማንኛውም አቅራቢ ክፍት ነው።
  6. አቅራቢዎች ጨረታውን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥን ገቢ የሚያደርጉበት ቀን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን ከቀኑ 8:00 ድረስ ይሆናል። ጨረታው በዚያኑ ከቀኑ 8:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል። ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሠዓት ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል።
  7. ተጫራቾች በጨረታው ደንብና መመሪያ መሰረት ጨረታውን ማቅረብ አለባቸው። ከጨረታው ደንብና መመሪያ ውጭ የሚቀርብ ማንኛውም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
  8. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለስልጣን

Summary
Central Ethiopia Region Roads Authority buys fixed electronic office equipment by open tender, open to any supplier regardless of nationality. Bidders need a relevant licence with taxes paid, supplier registration and VAT certificate.
Save Tender