Tender Detail

Tender Details


በአማራ ክልል የደቡብ ወሎ ዞን የጊምባ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ለባለበጀት መ/ቤቶች የፅህፈት መሳሪያ፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸርና የመኪና ስፔር ዕቃዎችን በ5 ሎቶች በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ያወጣው ማስታወቂያ (ቁጥር ጊ/ከ/አስ/ገ/361/2019)።

በደቡብ ወሎ ዞን የጊምባ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ጊ/ከ/አስ/ገ/361/2019

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የጊምባ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለሁሉም ባለበጀት መ/ቤቶች ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ሎት 1 የፅህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2 የፅዳት ዕቃዎች፣ ሎት 3 ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ሎት 4 ፈርኒቸር ዕቃዎችን እና ሎት 5 የመኪና ስፔር ዕቃዎች በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN No./ ያላቸው፣
  4. የግዥው መጠን ብር 500,000.00/አምስት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ/VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  6. የእቃዎቹን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔሲፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል በጊምባ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በግ/ፋ/ን/አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 4 ማግኘት ይቻላል።
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና/ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የዕቃዎቹን በየሎታቸው ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በጊምባ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ወይም ቢሮ ቁጥር 4 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን 07/03/2019 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናቶች በአየር ላይ ቆይቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ተዘግቶ፣ በዚሁ ቀን 4:00 ላይ ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል። ነገር ግን የመክፈቻው ቀን የበዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በዚሁ በተባለው ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
  10. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግዥና ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033-240-58-39 ወይም 033 240 5870 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

በደቡብ ወሎ ዞን የጊምባ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት

Summary
Gimba Town Finance Office (South Wollo, Amhara) buys in 5 lots for its budget offices: stationery, cleaning items, electronics, furniture and vehicle spare parts, by national open tender. Licensed suppliers with TIN and paid taxes; VAT for purchases of 500,000 birr and above.
Save Tender