Tender Detail

Tender Details


የኮምቦልቻ ሪጂዮፖሊታን ከተማ አስተዳደር አቢሻገር ክፍለ ከተማ አስተዳደር የፅህፈት መሳሪያዎች፣ የፅዳት እቃዎች፣ የደንብ ልብስና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን በ4 ሎቶች በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ያወጣው ማስታወቂያ።

አቢሻገር ክፍለ ከተማ አስተዳደር ኮምቦልቻ


ብሄራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በኮምቦልቻ ሪጂዮፖሊታን ከተማ አስተዳደር በአቢሻገር ክ/ከተማ አስተዳደር አገልግሎት የሚሆን ሎት 01 የፅህፈት መሳሪያዎች ሎት 02 የፅዳት እቃዎች ሎት 03 የደንብ ልብስ 04 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ በቀን 04/02/2019 የወጣውን ጨረታ በማየት ሰነዱን መግዛት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።

  1. በዘርፉ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት ያላቸው።
  2. የግዢ መጠኑ ከብር 500000/አምስት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ ተጫራቾቹ የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል።
  3. በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-7 ላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን በጨረታ መክፈቻው ቀንና ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ከተራ ቁጥር 1-2 ላይ የተጠቀሱትን ኦርጅናል ሰነድ ይዘው መቅረብ አለባቸው።
  4. ተጫራቾች ከሎት 1 እስከ ሎት 4 ላሉት ለእያንዳንዳቸው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በ CPO ብቻ የጠቅላላ ዋጋውን 1% ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
  5. ከተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ጸንቶ መቆያ ጊዜ የጨረታው ዋጋ ጸንቶ ከሚቆይበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ቢያንስ ለተጨማሪ 28 ጸንቶ ይቆያል።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ አቢሻገር ክፍለ ከተማ አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 12 በመምጣት በመክፈል ከ04/03/2019 እስከ 18/03/2019 ዓ.ም ዘወትር በስራ ሰአት 11:30 ድረስ መውሰድ ይችላሉ።
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶች ኦርጅናልና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ አቢሻገር ክፍለ ከተማ አስተዳደር ግዥና ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 12 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከወጣበት ከ04/03/2019 እስከ 18/03/2019 ዓ.ም 11:30 ድረስ መውሰድ ማስገባት ይችላሉ። የጨረታ ሳጥኑ በቀን 19/03/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ታሽጎ በዚሁ ቀን በ4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በግልፅ ይከፈታል። ይሁን እንጂ የጨረታ መክፈቻ ቀኑ በአል ከሆነና የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው የመክፈቻ ሰአት የሚከፈት ሆናል።
  8. አስፈላጊ ለሆኑ ዕቃዎች በክፍለ ከተማው ሳምፕል የሚያቀርብ በመሆኑ ሳምፕሉን በጥንቃቄ በማየት ዕቃዎችን ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  9. የጨረታው ውድድር የሚካሄደው በጥቅል ድምር ውጤት ስለሆነ የማይሞላ አይተም መኖር የለበትም ያልተሞላ አይተም ከተገኘ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ ይደረጋሉ።
  10. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ግልፅ ያልሆነ ነገር ሲያጋጥማቸው ጨረታውን ካወጣው አስሪው መስሪያ ቤት ጋር ጨረታ መክፈቻ 5/አምስት/ ቀን በፊት በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0914358368/0910193141 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
  11. የጨረታ ሰነዱ ላይ የድርጅቱ ማህተምና ፊርማ መደረግ ይኖርበታል ጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለው ከጨረታ ውድድር ውጭ የሰደረጋል።
  12. ጨረታው ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ የጨረታ ሰነዱ ከተከፈተበት ጊዜ በኋላ ለ45 ቀናት ይሆናል።
  13. ጨረታውን ለማዛባት የሞከሩ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ እንደሚሆንና ለወደፊቱም በመስሪያ ቤቱ ግዥ የማያሳትፍ እና ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚወረስ ይሆናል።
  14. ግዥ ፈጻሚው አካል ከአሸናፊው ተጫራች ጋር ውል ከመፈረሙ በፊት በአሸናፊው ተጫራች በውድድር የተገኘው ዋጋ ሳይቀየር በጨረታ ሰነዱ ከተገለጸው የአቅርቦት መጠን ላይ እስከ 20% (ሃያ በመቶ) መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል።
  15. የጨረታ አሸናፊው ድርጅት ንብረቱን አቢሻገርክፍለ ከተማ አስተዳደር ንብረት ክፍል ድረስ በራሱ ውጭ ማቅረብ የጠበቅበታል።
  16. ክፍለ ከተማው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አቢሻገር ክፍለ ከተማ አስተዳደር
ኮምቦልቻ

Summary
Abishager Sub-City Administration, Kombolcha city, buys in 4 lots: stationery, cleaning items, uniforms and electronics, by national open tender. Bidders need a renewed licence, paid taxes and TIN; VAT registration for purchases above 500,000 birr.
Save Tender