የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ጽ/ቤት ለአስተዳደሩ ተቋማት የጤና ባለሙያዎች ደንብ ልብስ፣ የስራ ደንብ ልብስና የደንብ ጫማዎችና የስራ መሳሪያዎችን በ3 ሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ያወጣው ማስታወቂያ (ቁጥር ግዥ/ን/ማ 512/የመ/ግ/ጨ/003/19)።
በድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨ/መ/ቁ ግዥ/ን/ማ 512/የመ/ግ/ጨ/003/19
በድሬዳዋ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ጽ/ቤት በ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት በአስተዳደሩ ስር ላሉ ተቋማቶች አገልግሎት የሚውል ሎት-1 የጤና ባለሙያዎች ደንብ ልብስ፤ ሎት-2 ለስራ አገልግሎት የሚውል ደንብ ልብስ እና ሎት-3 ለጤና ባለሙያዎች እና ለድጋፍ ሰጪዎች የሚውል የደንብ ጫማዎች እና የስራ መሳሪያዎች ግዢ በማእቀፍ ለመግዛት በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ማስታወቂያውን አውጥቶ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት:-
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- በተሰማሩበት የስራ ዘርፍ የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የጨረታ ሠነዱን በፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ቁጥር 109 ቀርበው ለእያንዳንዱ ሎት ብር500.00 (አምስት መቶ) መግዛት የሚችሉ ሲሆን በጨረታ መክፈቻው እለት የጨረታ ሠነዱን በትክክል ሞልተው ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዋናውንና ኮፒውን በአግባቡ አሽገው ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
- የጨረታ ሳጥኑ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሠዓት ላይ ታሽጎ በዛው ዕለት 4:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጽ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 215 በግልጽ ሲከፈት፤ ቀኑ በዓል ወይም የዕረፍት ቀናት ላይ ከዋለ በቀጣይ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን።
- ተጫራቾች ለሎት-1 ብር150,000.00 (አንድ መቶ ሃምሳ ሺ ብር) ፤ለሎት-2 ብር100.000.00 (አንድ መቶ ሺ ብር) እና ለሎት-3 ብር50,000.00 (ሃምሳ ሺ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ወይንም በጥሬ ገንዘብ ከጨረታ ሠነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- መሰሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጨማሪ ማብራሪያና መረጃ ቢያስፈልግ በሚመለከተው አድራሻ መጠቀም ይችላሉ። በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ጽ/ቤት ቢሮቁጥር 215
የስልክ ቁጥር:- 0915-76-19-64 / 0923-32-32-42
ድሬዳዋ
በድሬዳዋ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ጽ/ቤት
Summary
Dire Dawa Administration Public Procurement and Property Disposal Service buys, under a framework, uniforms for health professionals, work uniforms, and shoes and work tools for health and support staff in 3 lots. Licensed, VAT-registered suppliers may bid.
